ሰላም ሰዎች ይህን ጥያቄ ከዚህ በፊት ጠይቄ ነበር እና አሁን ሴቶች መልሱልኝ እባካቹ ተባበሩን ..ከልጅቷ እንዳልኩት ሆነ በጣም ወደድኳት እሷ ጋም ይህ ስሜት ያለ ይመስለኛል ግን ያጠራጥራል እንዴት ነው ላውቅ ልረዳ ምችለው ስሜቷን??? ከተግባሮቿ ከንግግሮቿ?? እሷ ጋ ይኑር አይኑር እንዴት ልወቅ??? ቀድሜ መንገሬስ ጥሩ ነው?????
ሰላም ሰዎች ምክራቹ ያስፈልገኛል በጣምምምም ፤ ምን መሰላቹህ ከሆነች ልጅ ጋ ተዋወቅን እና ጥሩ እናወራለን ጥሩ ተቀራርበናል ልጅቷ በሀይማኖቷ ጠንካራ ጎበዝ ናት እኔ ደግሞ በተቃራኒው ደካማ ነኝ መፅሀፍ ቅዱስ ራሱ አንብቤ አላቅም እና በሷ ምክንያት ማንበብ ጀመርኩ እሷ ይህን አንብብ ይህ እንዲ ነው እያለች እየነገረችኝ እያስረዳችኝ ማለት ነው፤... እና በጣም እየለመድኳት እየቀረብኳት ማይሆን ነገር ውስጥ እየገባው ነው ( እራሴን ከ እንደዚህ አይነት ግንኙነት/ የፍቅር ስሜት ካራኩኝ በጣምም ቆይቻለው ) በሷ ምክንያት ማንበብ ጀመርኩ ይህን ያህል ተፅህኖ ፈጥራብኝ ፡ በሷ የጀመርኩትን ነገር እሷን ሳጣ ጠባሳ፣ህመም እንዳይሆን ይባስ ጭራሹን ከድሮ የባሰ ከሀይማኖቴ እንዳያርቀኝ ፈራው... እና እሷን ከነ አካቴው ርቄ ከቻልኩኝ በራሴ ለማንበብ ለመለወጥ ካልሆነ ልትወው አሰብኩ ምን ትመክሩኛላቹ ምን ላርግ