ሰላም ሰዎች ምክራቹ ያስፈልገኛል በጣምምምም ፤ ምን መሰላቹህ ከሆነች ልጅ ጋ ተዋወቅን እና ጥሩ እናወራለን ጥሩ ተቀራርበናል ልጅቷ በሀይማኖቷ ጠንካራ ጎበዝ ናት እኔ ደግሞ በተቃራኒው ደካማ ነኝ መፅሀፍ ቅዱስ ራሱ አንብቤ አላቅም እና በሷ ምክንያት ማንበብ ጀመርኩ እሷ ይህን አንብብ ይህ እንዲ ነው እያለች እየነገረችኝ እያስረዳችኝ ማለት ነው፤... እና በጣም እየለመድኳት እየቀረብኳት ማይሆን ነገር ውስጥ እየገባው ነው ( እራሴን ከ እንደዚህ አይነት ግንኙነት/ የፍቅር ስሜት ካራኩኝ በጣምም ቆይቻለው ) በሷ ምክንያት ማንበብ ጀመርኩ ይህን ያህል ተፅህኖ ፈጥራብኝ ፡ በሷ የጀመርኩትን ነገር እሷን ሳጣ ጠባሳ፣ህመም እንዳይሆን ይባስ ጭራሹን ከድሮ የባሰ ከሀይማኖቴ እንዳያርቀኝ ፈራው... እና እሷን ከነ አካቴው ርቄ ከቻልኩኝ በራሴ ለማንበብ ለመለወጥ ካልሆነ ልትወው አሰብኩ ምን ትመክሩኛላቹ ምን ላርግ
Jan 10, 2026የዚህን ያህል ራስህን ለምን ታስጨንቃለህ...ምናልባት ፈጣሪ ላንተ ያላት ሴት ትሆናለች ለምን ትርቃታለህ..ያንተ መሆን ካልቻለች ደሞ በቃ በህይወት ውስጥ ሚያጋጥመን ነገር ነው ምናልባት በህይወትህ ውስጥ አንተ እንድትለወጥ ምክኒያት ሆና ካለፈች እሱም አንድ ነገር ነው....በፊት ደካማ ከነበርክ ደሞ ምንም ምታጣው ነገር ያለ አይመስልም...አትራቃት ተለወጥባት
Jan 10, 2026