#Day_4 ዛሬ ሁሉንም ነገር ልጋፈጠው ነው ሁሉንም ትቼ የ 50 ባለቤቴን ጭምር በእርግጠኝነት ልቤን ጭንቀት አጥልቼ ቤተሰቦቼን ተመልክቼ ተሰናበትሁ። ማንም አላወቀም፤ ቃል አልተናገርኩም። ሌሊቱ ሲወርድ ወደ እርሻው ተመለስሁ። መሬቱ ቀዝቃዛ ነበር፣ ነገር ግን ከታች የሚመጣ ሙቀት እንደ አንድምታ ይመታ ነበር። ያ መብራት እንደ ዓይን ተከፍቶ ተመለከተኝ። እንደ አንድምታ መመታቱ በጣም ጠነከረ፤ መሬቱ ተከፈተ። እውነቱ ተገለጠ፤ መብራቱ ነገር አይደለም፣ ሕያው ነበር። ከመሬቱ ሥር የሚኖር ምስጢር —የእኛን ፍርሃት የሚመገብ፣ ሰውን በማስጠራት የሚያድግ። ያቺ ሜትር ከዘጠና እንስት እኔን አላዳነችኝም፤ ምልክት አድርጋ መለሰችኝ እንጂ ። እኔ ነበርኩ የተመረጥሁት ይሄንን ድል ።በመጨረሻ እውነቱን ተቀበልሁ፤ መሄዴ መመለስ አይደለም ነበር። መብራቱ ውስጤ ገባ፣ ድምፁ እኔ ሆነ። እርሻው ጸጥ አለ፣ ነገር ግን ከዚያ ሌሊት ጀምሮ በሩቅ ሰዎች የሚያዩት መብራት እኔ ነኝ። አሁን ግን ውስጤ ተጠራጠረ ምናልባት የ አካባቢው ሰው እኔ ይህን እንዳላይ ለምን ፈለገ? ለምንስ እኔን? ከዚ ቡሃላስ ማንን ነው የማምነው ማንን ነው የኔ የምለው? ምን ታስባላችሁ አውቀው ነው ደበቁኝ? እና ሰዎቹን ከዚህስ ቡሃላ ልመናቸው?
#Day_3 በመጨረሻ ውሳኔ ወስኜ ዛሬ ሌሊት ብቻዬን ወደ እርሻው ተመለስሁ። ያ መብራት ይህን ጊዜ ቀድሞ ከማየቴ ይልቅ ቀርቦ ተገለጠ፣ እንደ ሕይወት የሚመታ ይመስል ነበር። ድምፁ ቆመ፣ ጸጥታ ሁሉን ሸፈነ። እኔ ግን እግሮቼን አንስቼ አንድ እርምጃ ብቻ ቀረብሁ በዚያን ጊዜ መሬቱ እንደ ልብ ተመታ። ሁሉም ነገር ተንቀጠ እኔም በ ሃሳብ ጠቆርኩ አጠርኩ ወፈርኩ ምን ይዋጠኝ? ከርቀት አንድ ጠቆር ብላ አጠር ያለች ወፈር ብላ አጠር ያለች ቁመቷ ወደ ሜትር ከ ዘጠና የሚገመት እንስት መጣ ጎተተችኝ ሰባ ከ ሀገሬ አስገባችኝ ቤተሰቦቼን አገኘሁ ደስታ ተሰማሁ አሁን ግን ወደ ቦታው ለመሄድ ሳስበው ይጨንቀኛል ይረብሸኛል ምን ባደርግ ነው የሚሻለው እናንተ ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር ቤተሰቦቻችሁን ጥላቹ ትጋፈጡታላቹ? ወይስ ቤተሰቤን አርፌ ስራ እየሰራሁ ላስተዳድር? መልሳችሁን እሻለሁ አመሰግናለሁ