#Day_3 በመጨረሻ ውሳኔ ወስኜ ዛሬ ሌሊት ብቻዬን ወደ እርሻው ተመለስሁ። ያ መብራት ይህን ጊዜ ቀድሞ ከማየቴ ይልቅ ቀርቦ ተገለጠ፣ እንደ ሕይወት የሚመታ ይመስል ነበር። ድምፁ ቆመ፣ ጸጥታ ሁሉን ሸፈነ። እኔ ግን እግሮቼን አንስቼ አንድ እርምጃ ብቻ ቀረብሁ በዚያን ጊዜ መሬቱ እንደ ልብ ተመታ። ሁሉም ነገር ተንቀጠ እኔም በ ሃሳብ ጠቆርኩ አጠርኩ ወፈርኩ ምን ይዋጠኝ? ከርቀት አንድ ጠቆር ብላ አጠር ያለች ወፈር ብላ አጠር ያለች ቁመቷ ወደ ሜትር ከ ዘጠና የሚገመት እንስት መጣ ጎተተችኝ ሰባ ከ ሀገሬ አስገባችኝ ቤተሰቦቼን አገኘሁ ደስታ ተሰማሁ አሁን ግን ወደ ቦታው ለመሄድ ሳስበው ይጨንቀኛል ይረብሸኛል ምን ባደርግ ነው የሚሻለው እናንተ ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር ቤተሰቦቻችሁን ጥላቹ ትጋፈጡታላቹ? ወይስ ቤተሰቤን አርፌ ስራ እየሰራሁ ላስተዳድር? መልሳችሁን እሻለሁ አመሰግናለሁ
ከዚያ ምሽት በኋላ ያ ያልታወቀ መብራት በተደጋጋሚ መታየት ጀመረ። በመጀመሪያ ነገር የእኔን ልብ በጣም አስፈራኝ፣ ነገር ግን ቀስ በቀስ የምርምር ፍላጎቴ ጨመረ። የሰፈሩ ሰዎች በምሽት ከዚያ ቦታ እንዳንቀርብ እያስጠነቀቁኝ ነበር፣ እነሱም ስለዚያ ቦታ ሲናገሩ ፊታቸው ይቀየር ነበር። አንድ ሌሊት ግን የተለየ ነገር ተከሰተ። ነፋስ አልነበረም፣ ሰማይም ጸጥ ነበር፣ ነገር ግን ከእርሻው መካከል ዝቅተኛ እና እየተደጋገመ የሚመጣ ድምፅ ሰማሁ። እንደ ነፍስ መተንፈስ ያለ ይመስል ነበር፣ አንዳንዴም እንደ እንስሳ መንቀሳቀስ። እግሮቼ መንቀሳቀስ አልቻሉም፣ ነገር ግን ዓይኖቼ ቦታውን ተመልክተው ቆዩ። ከዚያ በኋላ መቆየቴ የቀድሞ እንዳልነበር ሆነ። መሄድ እፈልግ ነበር፣ ነገር ግን አጎቴንና ሥራዬን መተው አልቻልኩም። እንዲሁም እውነቱን ማወቅ የማይታገስ ፍላጎት ሆነብኝ። ደግሜ ወደ ቦታው ሄጄ ሁኔታውን እና ምንነቱን ላጣራ ወይንስ ቤተሰቦቼን ይዤ ወደ ሩቅ ሀገር ልኮብልል