ማወቅ የፈለኩት ከእሷ ጋር መቀጠል አለብኝ ወይስ የለብኝም የሚለውን አይደለም። የእምነት ልዩነት ኖሮን አልቀጥልም። ነገር ግን የሁለቱም እምነት ተከታዮች ካላችሁ የሁለቱንም ትክክለኛ የአስተምህሮ ልዩነት መረዳት እፈልጋለሁ።
እዴት ናቹ ፍቅረኛዬ ኦርቶዶክስ ቅባት እኔ ደግሞ ተዋሕዶ አማኝ ነኝ። በጣም እወዳታለሁ ትወደኛለች። ግን እምነት ሊለያየን ነው። በሁለቱ እምነቶች መካከል በዋናነት ያለው የምስጢረ ሥጋዌ ልዩነት ነው። ተዋሕዶዎች ቅባቶችን የተረዳንበት መንገድም ትክክል አይደለም። ተዋሕዶዎች "የቅባት አስተምህሮዎች ቃል ከሥጋ ጋር ሲዋሐድ የባሕርይ ክብሩን እንዳጣ፣ በዮርዳኖስ ጥምቀት ጊዜ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በርሱ ላይ በመውረድ (በመቀባት) ወደ ክብሩ እንደተመለሰ ያስተምራሉ" ይላሉ። ቅባቶችን ስጠይቃቸው ደግሞ እንደዚኽ ብለው እንደማያምኑ ይነግሩኛል። እና በሁለቱ መካከል ያለውን ትክክለኛ ልዩነት ማወቅ እፈልጋለኹ። የሁለቱም እምነት ተከታዮች ካላችኹ ልዩነታችኹን አስረዱኝ። ላጣት አልፈልግም እና በጭንቀት ልሞት ነው።