እዴት ናቹ ፍቅረኛዬ ኦርቶዶክስ ቅባት እኔ ደግሞ ተዋሕዶ አማኝ ነኝ። በጣም እወዳታለሁ ትወደኛለች። ግን እምነት ሊለያየን ነው። በሁለቱ እምነቶች መካከል በዋናነት ያለው የምስጢረ ሥጋዌ ልዩነት ነው። ተዋሕዶዎች ቅባቶችን የተረዳንበት መንገድም ትክክል አይደለም። ተዋሕዶዎች "የቅባት አስተምህሮዎች ቃል ከሥጋ ጋር ሲዋሐድ የባሕርይ ክብሩን እንዳጣ፣ በዮርዳኖስ ጥምቀት ጊዜ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በርሱ ላይ በመውረድ (በመቀባት) ወደ ክብሩ እንደተመለሰ ያስተምራሉ" ይላሉ። ቅባቶችን ስጠይቃቸው ደግሞ እንደዚኽ ብለው እንደማያምኑ ይነግሩኛል። እና በሁለቱ መካከል ያለውን ትክክለኛ ልዩነት ማወቅ እፈልጋለኹ። የሁለቱም እምነት ተከታዮች ካላችኹ ልዩነታችኹን አስረዱኝ። ላጣት አልፈልግም እና በጭንቀት ልሞት ነው።
Aug 31, 2026ብራዘር ቅባቱ አንተ ነህ እንዴ 😆 በል አስጠምቃት አልያ አሰናብታት
Aug 31, 2026