ሰላም እንዴት ናችሁ ጥያቄው ለሙስሊሞች ነው ባለፈው ጠይቄ አልመለሳችሁልኝም ነበር እነዚህን 8ቱን ጥያቄ እና አስረዱኝ በተለይ ስለማታውቁት እና ስላልተረዳችሁት መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስትሮጡ ለነበራችሁ ይሄ ጥያቄዎች ከቁርአን አንጻር ስለሆነ መልሱልኝ ⚠ማሳሰቢያ ያህል ◉ ከተጠየቀው ውጪ ሌላ የማይገናኝ ነገር ለመመለስ እንዳትደክሙ ዝምብሎ ዝርግፍ አርጎ ከAI ለማምጣት አትድከሙ ፖይንቱን ብቻ ግልጽ አጭር እና ቀለል ባለ መንገድ መልሱ ◉ ጥያቄ እንዳትዘሉ ◉ ከጠየኩት እሱም ከቁርአን ብቻ እና ታሪክ ያልኩትን ከሱ ውጪ ሌላ ቦታ እንዳትዳክሩ ቁርአን ለሁሉም ነገር መልስ አለው እና በቂ ነው ብላችሁ ምታስቡ ከሆነ ◉ አደራ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ለመለጠፍ እንዳትሞክሩ ለማምለጥ ካልሆነ በስተቀር ◉ የማይሆን ሌላ ወሬ እና ሌላ Topic መዛችሁ ሀሳብ ለማስቀየር እንዳትሞክሩ ብዙ ማሳሰብ ይቻላል ግን በአጭሩ የተጠየቃችሁትን ብቻ መልሱ ሌላ ነገር ውስጥ እንዳትገቡ የማታውቁ አትድከሙ just🤐 ⚠ ማሳሰብያውን ጥሳችሁ ዝምብላችሁ የማይገናኝ ነገርን ለደከማችሁ ሰዎች አዝናለው እኔም አልደክምም በደምብ እንደምታስረዱኝ ተስፋ አደርጋለው አመሠግናለሁ 🙏
ጥያቄ ለሙስሊሞች 1. በኢሳ ፋንታ የተሰቀለው ሰው ማነው ? ብዙ ምልከታ ስላለ የዛ ሰው መጨረሻውስ እንዴት ነው ? 2. ቁርአን ከመውረዱ በፊት የእውነት እስልምና እራሱ ከነበረ ኢየሱስ አልተሰቀለም ብሎ ያስተማረ ሰው እና የተፃፈ ነገር ካለ ብታሳዩን ? በተለይ ከኢሳ እስከ መሐመድ ባለው ጊዜ ውስጥ 3. አላህ ኢሳን ለምን እንዲው አያድነውም ነበር ሌላ ሰው ማስገደል ለምን አስፈለገ ? 4. አስመስሎባቸው ከሰቀሉት በኋላ ሰቀልን ያሉትን ረገምናቸው ይላል ይሄ ሴንስ ይሰጣል ? ልክ አይደሉም ስለተመሰለባቸው ? 5. በኢሳ ካስመሰለባቸው እንዴት ሐዋርያቱንም እና እናቱንም ጭምር ይሸውዳል እነሱ ላይም አስመሰለባቸው ? ሐዋርያትም ተሰቅሏል ሞቷል እያሉ አስተማሩ(የታሪክ ምስክርነት አለን በታሪክም ይታወቃል) 6. አይሁዶችም ክርስቲያኖችም ተጠያቂ አይደሉም ምክንያቱም አላህ ስላስመሰለባቸው እውነት ኢየሱስ ባይሰቀል ባይሞት እና ባይነሳ ኖሮ ሐዋርያት ለውሸት ብለው እስከሞት ድረስ ተነስቷል እያሉ ይሰብኩ ነበር ?(የታሪክ ምስክርነት አለን) 7. ኢየሱስ ካልተሰቀለ ይሄን ለመመስከር 600 ዓመት ምን አስጠበቀ ? በነዚህ አመታት ውስጥ ተሰቀለ ብለው እንግዲ በቁርአኑ እምነት የሳቱ ስላሉ 8. እስልምና ሁሌ ከታሪክ ጋር ሚጋጨው ለምንድነው ? በተለይ በስቅለት ጉዳይ ኢየሱስ እንደተሰቀለ(የታሪክ ምስክርነት አለን ከክርስትና ውጪ ባሉ የታሪክ ጸሐፊያን እና ጠቢባን)