አንደምን ከረማችሁ ከዚህ በፊት በግሌ ላይብረሪ በማቋቋም በነፃ አገልግሎት መስጠት እንደምፈልግ ነግሬያችሁ መልካም ምክርን ለግሳችሁኛልና፤ በስጦታ የተበረከቱ የመማሪያ መፅሐፍትን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ፈልጌ በግሌ ባመጣ ቀረጥ እንደሚያስከፍለኝ ግን ከ ትምህርት ተቋም ጋር በመሆን ብቻ በነፃ ሊገባ እንደሚችል ነግረውኝ ተገርሜያለሁ። ዊስኪና ሲጋራን ዲዩቲ ፍሪ እያመጣን የመማሪያ መፅሐፍ መቀረጡ ሲገርመኝ፤ የትምህርት ተቋማት መፅሐፉን እንዲያስገቡልኝ ብጠይቅ ደግሞ የጠየቁት ገንዘብ እንዳዝን አድርጎኛል። ሌላ መፅሐፍቶችን ማስገባት የምችልበት መንገድ ካለ ብትጠቁሙኝ ስል ቀና ትብብራችሁን እጠይቃለሁ።
በአከባቢዬ ላይ ለልጆችም ሆነ ለወጣቶች ማንበቢያ ስፍራ የለም እና ነፃ ላይብረሪ ሰፈር ወስጥ መክፈት እፈልጋለው። እናም ይህን ለማድረግ ከቀበሌ ንግድ ፈቃድ/ ምዝገባ ያስፈልጋል ወይ? እዚህ ሀገር የግል ላይብረሪ አላይም የምታውቁ ካላችሁ አማክሩኝ እስቲ