በአከባቢዬ ላይ ለልጆችም ሆነ ለወጣቶች ማንበቢያ ስፍራ የለም እና ነፃ ላይብረሪ ሰፈር ወስጥ መክፈት እፈልጋለው። እናም ይህን ለማድረግ ከቀበሌ ንግድ ፈቃድ/ ምዝገባ ያስፈልጋል ወይ? እዚህ ሀገር የግል ላይብረሪ አላይም የምታውቁ ካላችሁ አማክሩኝ እስቲ
Nov 16, 2021እኔም በከተማ ደረጃ ላይብረሪ አጥቼ በጣም ደንቆኝ ነበር ። ግን ለዚህ ችግር ምንም እርምጃ አልወሰድኩም። አንተ እንደዚ ማሰብህ በጣም ጥሩ ነው ። የአዋቂ ሰው አስተሳሰብ ነው። ያው አገልግሎቱ ምንም አይነት ሽያጭ ስለሌለው ንግድ ፍቃድ የሚያስፈልገው አይመስለኝም። ለምን ንግድ ስላልሆነ ። ምናልባት የቀበሌ አስተዳደሩ ቦታ እና አንዳንድ እጋዛዎችን ሊያረጉልህ ይችላሉ። እናም መጽሀፍትን ምታሰባስብ ከሆነ እኔ ጋር የተወሰኑ አሉ እነሱም መስጠት እችላለሁ።
Nov 16, 2021