መኖር ማለት ለናንተ ምን ማለት ነው? በስጋ መኖር ነው ወይስ በሰዎች ልብ? Socrates በህይወት አለ ወይስ የለም?
#3 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ ምድርም ባዶ ነበረች ፥ አንዳችም አልነበረባትም ፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበር ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላየ ሰፍፎ ነበር። እግዚአብሔርም ብርሃን ይሁን አለ ፤ ብርሃንም ሆነ። ዘፍጥረት 1 ፥ 1-3 ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ ፥ ሦስተኛ ቀን። እግዚአብሔርም አለ። ቀንና ሌሊት ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ ፤ ለምልክቶች ለዘመኖች ለእለታት ለዓመታትም ይሁኑ ፣ እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ ፤ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሰለጥን ፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን፤ ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ። ዘፍጥረት 1 ፥ 13-16 እሺ ይህን አስረዱኝ ፀሀይ ከብርሃን በዋላ ወይስ ብርሃን ከፀሀይ በዋላ? እሺ ውሃ ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ ሰፍፎ ነበር ከተባለ ውሃ እግዚአብሔርን ይቀድማል ማለት ነው?