#3 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ ምድርም ባዶ ነበረች ፥ አንዳችም አልነበረባትም ፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበር ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላየ ሰፍፎ ነበር። እግዚአብሔርም ብርሃን ይሁን አለ ፤ ብርሃንም ሆነ። ዘፍጥረት 1 ፥ 1-3 ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ ፥ ሦስተኛ ቀን። እግዚአብሔርም አለ። ቀንና ሌሊት ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ ፤ ለምልክቶች ለዘመኖች ለእለታት ለዓመታትም ይሁኑ ፣ እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ ፤ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሰለጥን ፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን፤ ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ። ዘፍጥረት 1 ፥ 13-16 እሺ ይህን አስረዱኝ ፀሀይ ከብርሃን በዋላ ወይስ ብርሃን ከፀሀይ በዋላ? እሺ ውሃ ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ ሰፍፎ ነበር ከተባለ ውሃ እግዚአብሔርን ይቀድማል ማለት ነው?
#2 እግዚአብሔር/አላህ አዳምንና ሄዋንን ሲፈጥር እፀ በለስን መፍጠሩ ምን ማለት ነው? ሌላው ገነት/መንግስተ ሰማያት ላይ ፍፁም ደስታ አለ። መንም ሀዘን የለም የሚሉት ነገር... ቆይ ያለ ሀዘን ደስታ ራሱ እንዴት ይገኛል? ያለ ስጋስ ምን አይነት ደስታ ሊኖር ነው? ምንመገበው ምግብ መና ነው። እንዴ መንፈስም ምግብ ይበላል? ነፃ ሚሉት ነገር አለ.... አንዱ አንስቶ ነበር... ለኔ በመፅሀፍ ቅዱስ መሰረት ነፃ ፍቃድ ሚባል ነገር ፌክ ነው። አንድ ቤተሰብ ለልጁ ነፃ ፍቃድ ሚሰጥ ከሆነ ገነቱንም ሲኦሉንም ሚፈጥረው ልጁ ነው። ነገር ግን ሲአልንም ገነትንም የፈጠረው አላህ/እግዚአብሔር ሆኖ እንዴት ነፃ ፍቃድ አለ ልንል እንችላለን? እሺ ቆይ ገነት በምድር ነበር አሉ😂 እነ አዳም ወደዛ ሊመለሱ ሲሉ ነበልባል አለ በዛም መላእክት ይጠብቃሉ... አዳም ለልጆቹ ሳይጠቁም ሄዶ ነው ወይስ ገነት ተነነች?