#2 እግዚአብሔር/አላህ አዳምንና ሄዋንን ሲፈጥር እፀ በለስን መፍጠሩ ምን ማለት ነው? ሌላው ገነት/መንግስተ ሰማያት ላይ ፍፁም ደስታ አለ። መንም ሀዘን የለም የሚሉት ነገር... ቆይ ያለ ሀዘን ደስታ ራሱ እንዴት ይገኛል? ያለ ስጋስ ምን አይነት ደስታ ሊኖር ነው? ምንመገበው ምግብ መና ነው። እንዴ መንፈስም ምግብ ይበላል? ነፃ ሚሉት ነገር አለ.... አንዱ አንስቶ ነበር... ለኔ በመፅሀፍ ቅዱስ መሰረት ነፃ ፍቃድ ሚባል ነገር ፌክ ነው። አንድ ቤተሰብ ለልጁ ነፃ ፍቃድ ሚሰጥ ከሆነ ገነቱንም ሲኦሉንም ሚፈጥረው ልጁ ነው። ነገር ግን ሲአልንም ገነትንም የፈጠረው አላህ/እግዚአብሔር ሆኖ እንዴት ነፃ ፍቃድ አለ ልንል እንችላለን? እሺ ቆይ ገነት በምድር ነበር አሉ😂 እነ አዳም ወደዛ ሊመለሱ ሲሉ ነበልባል አለ በዛም መላእክት ይጠብቃሉ... አዳም ለልጆቹ ሳይጠቁም ሄዶ ነው ወይስ ገነት ተነነች?
ስለ እግዚአብሔር ነው ምጠይቀው! ብዙን ጊዜ ሀይማኖቶች ፈጣሪ ሁሉ ቦታ አለ ይላሉ። ይህ ማለት ደግሞ ሁሉንም ያያል ይሰማለሰ ማለት ነው። አንዳንድ ፈላስፎች ግን እንደ something which occupy space አድርገው ስለሚያስቡ ሁሉም ቦታ እግዚአብሔር ስላለ ሴጣን እዛ ቦታ መገኘት አይችልም ይላሉ። That means በሌላ አነጋገር እውነት ባለበት ውሸት አይገኝም። ለኔ ግን ይህ ልዩ ነው ምናልባት ጥሩ እና መጥፎ መንፈስ አለ ግን እግዚአብሔር እና ሴጣን ሚባለው ነገር ውሸት ይመስለኛል። እስቲ አስቡ ከሰው በላይ ይራራል የተባለው እግዚአብሔር ሁሉ ቦታ አለ ከተባለ አንድ ሰው ሲርበው ምግብ ሊሰጠው ይችላል ፤ እራሱነሰ ሊያጠፋ ሲል ይከላከላል ፤ በቸገረው ጊዜ ያግዘዋል አልያም ሴጣን እና ክፋትን ከነ አካቴው ያጠፋል። ለምሳሌ ስለ ዳንኤል ፀሎት እናውራ የዳንኤል ፀሎት ፈጣሪ ጋር ከመቶ ምናምን ቀን በዋላ ደረሰ ይባላል። ይህ ማለት ደግሞ እግዚአብሔር ሁሉም ቦታ የለም ማለት ይሆናል አልያም ሴጣን ከለከለው ከተባለ ሴጣን ከእግዚአብሔር ጋር ሚያተካክለው ሀይል አለው ማለት ነው። እኝን ሁሉ ስናይ ስለ እግዚአብሔር Existence ጥርጣሬ ይኖረናል ማለት ነው። ምናልባት ሰዎች eternal lifeን በdeath ፍርሀት የፈጠሩት ድርሰት ይሆናል። እስቲ ሀሳባችሁን አጋሩኝ እኔ ሙሉ በሙሉ ሀይማኖቴን እየካድኩ ነው። i am orthodox!