Amstu(5) amade mistirat yemibalut kene mabrariyachew orthodox aschekuay new please
Aug 09, 2021በ 40 እና በ 80 ቀን ምንጠመቅበት ምክንያት #እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ በ40 ቀኑ ሔዋንን ደሞ በ80 ቀኑዋ ነው ወደ ዘላለም ቤታችን ወደ ገነት ያስገባቸው። እኛም እሱን ምሳሌ አርገን ወንድ በ40 ሴት በ80 እንጠመቃለን። ይህንንም #መፅሀፈ_ኩፋሌ 4:9 ላይ በግልፅ ታገኘዋለህ። ለምን እንጠመቃለን ለሚኘው ደሞ 1. ድኀነት በጥምቀት ስለሆነ ነው ማር 16:16 "ያመነ የተጠመቀ ይድናል፣ ያላመነ ግን ይፈረድበታል" 2. በጥምቀት ከውሀና ከ #መንፈስ_ቅዱስ ዳግም እንወለዳለን፣፣ ዮሀ 3:3-6 " እውነት አውነት እልሀለው ሰው ከ ውሀና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ #እግዚአብሔር መንግስት አይገባም" በዚህም ላይ ቲቶ 3:5 ላይ ተጨማሪ መልስ ስላለ አምብበው። 3. በጥምቀት የሀጢያት ስርየት ስለሚደረግ እንጠመቃለን ሐዋ 22:16 "አሁንስ ለምን ትዘገያለህ? ተነስና ሰሙን እየጠራህ ተጠመቅ ፣ ከ ሀጢያትህም ታጠብ" ሌላው በ በዓለ ሀምሳ በ ቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት ልቦናቸው ከተመሰጠው አንዳንዶቹ "ምን እናድርግ" ባሉት ጊዜ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ የመለሰላቸው " ንስሀ ግቡ ኃጥያታችሁ ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በ#እየሱስ_ክርሰቶስ ስም ተጠመቁ" (ሐዋ 2:37-38)ብሏቸዋል። 4. በጥምቀት ከ ጌታችን ከ #እየሱስ_ክርስቶስ ጋር አንድ እንሆናለን። ገላ 3:27 "ከ#ክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃቹ ሁሉ #ክርስቶስን ለብሳችኂልና" ምስጢር የተባለው እኮ ከምዕመኑ እንዲደበቅ አይደለም በየ ቤተክርስቲያኑ ትምህርቱ በሁሉም የ ኦረቶዶክስ ስረዓቶች ላይ ይሰጣል እኮ። መከታተል የኛ ፋንታ ነው።
Aug 10, 2021