አሁን የዲፕ ተማሪ ቀጣይ ተመራቂ ነኘ ምን መሰላችሁበጣም አብዝቼ የማስበውና የምመኝው ነገር ብዙ ነገር ወደኔ እድል ሁኖ ይመጣልኛል እግዛብሄርን ባማር እራሱ የሚስቅብኝ ይመስለኛል በቃ መማር የምፈልጋቸው ነገሮች በነፃ የአጭር ኮርስ መስራት የፈለኩትን በቀጥታ ሊያሰሩኝ ከሚችሉ ሰዎች ጋር እድሉን የማግኝት አሁን በቅርብ እንኳን vocal መማር ፈልግ ነበር ከዛ የደሀ ልጅ ስለሆንኩ ብር አጣሁ በትርፍ ጊዜየ ለመማር ከዛ ብሄራዊ ቲያትር ማስታወቂያ አውጥቶ ነበር ተመዘገብኩ እሚገርማችሁ ድንገት ሼር የተደርገ ፌስቡክ ስከፍት ነው ያየሁት ለዛውም የመጨርሻ ቀን ነበር መመዝገቢያ እና አሁን መሄድ አስጠላኝ በባህሪየ ከቤት መውጣት አልወድም በርግጥ አስተዳደጌም ነው እና በቃ ከቤት ባለመውጣት ምክንያት በጣም ህይወቴን ሊቀይሩ የሚችሉ ነገሮችን እያጣሁ ነው በቃ አሁን አሁን በጣም በራሴ ተስፍ እየቆርጥኩ ነው አዲስአበባ ውስጥ እራሱ የምኖር አልመስልም ቦታዎችን አላቅም እና ምን ላርግ ድህነቴ አብሮኝ ሊቀጥል ነው ብዬ ፈራለሁ
Aug 07, 2021ሰዎች ማለት ትላልቅ ሰዎች ke65 በላይ ያሉ ሰዎች ላይ የተሰራ ጥናት ነበር እሱን ብነግርሽ የበለጠ ይገልፅልኝ ይሆናል... ጥናቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ነው የሚያካትተው በዓለም ዙርያ የተደረገ ጥናት ነው:: ሁሉም አንድ ጥያቄ ይጠየቃሉ እና ጥያቄው የሚለው 'በሕይወታቹ የሚፀፅታችሁ ምንድነው' የሚል ነበር:: አንዳንዱ ከቤተሰብ ጋ ጊዜ አለማሳለፍ ይላሉ አንዳንዱ መናገር ሲኖርብኝ ያልተናገርኩት ብቻ የተለያየ ነገር ተናገሩ ነገር ግን በሰሩት ስህተት ወይም ጥፋት አልነበረም አብዛኛው የሚፀፀተው:: ስላልሰሩት ነገር ነው ሰዉ ሚያዝነው የሚያንገበግበው:: ጊዜ አይመለስም በ20ዎቹ የምትሰርያቸወን በ30ዎች አትሰሪም ብትሰሪም እንደዛ አይሆንም... ዛሬ የሚመጡት ነገ ላይመለሱ ይችላሉ አንቺ ራሱ በአስራዎች ሃያዎች ያለሽ መልክ ተነሳሽነት ፍላጎት አቁአምሽ ሁላ ይቀየራል:: ዛሬ ስትጀምሪ ግን ቀን በቀን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየትሻሻልሽ ነው ምትመጪው:: ዛሬ ምናልባት በ20ዎቹ መጀመሪያ ልትሆኚ ትችያለሽ ዛሬ ወተሽ አዲስ አበባን ካላየሽ ግን ስትቆይ መውጣትሽ አይቀርም ማየትሽ አይቀርም የዛኔ በ30 በ40 አመትሽ ካላወቅሽ የትልቅ ሕፃን ነው የምትሆኚው እሱ ደሞ በጣም በጣም ቀፋፊ ነገር ነው::
Aug 08, 2021