እንደዛ ከሆነ ፈጣሪ ሁሉን ይችላል የሚሉ ሰዎች እንዲህ ብለው መመለስ ይችላሉ....ፈጣሪ ሁሉን ስለ ሚችል በአንድ ጊዜ እሱ ማንሳት የማይችለውን ድንጋይ መፍጠርም፣ ያንኑ ድንጋይ ማንሳትም ይችላል። ምክንያቱም ሁሉን የሚችል ስለሆነ በአንድ ጊዜ ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን አስማምቶ ማድረግ ይችላል። ሁሉን ቻይነቱ የተገደበ ስላልሆነ ተቃራኒ ነገሮችንም በአንድ ጊዜ አንድ ላይ ማከናወን ይችላል። እንዴት ብሎ የሚጠይቅ ካለ ፈጣሪ ሁሉን ማድረግ ይችላል ብለን እንመልሳለን። መጋቢ ሐዲስ እሸቱ እንዲህ ይላሉ:- "እግዚአብሔር ከእኛ የስሜት ሕዋስ ቁጥጥር በላይ ነው"! በተገደበ የማሰብ አቅማችን የፈጣሪን ያልተገደበ ሁሉን ቻይነት ለመመርመር መነሳታችን በራሱ ስህተት ነው።
Aug 06, 2021