ሰላም እንዴት ናችሁ ጥያቄየ ምን መሰላችሁ 19አመቴ ነው እና ከሰው ጋር ልግባባ አልቻልኩም ለምሳሌ ቴሌግራም ፊስቡክ ላይ የሚመጡትን ያሉኝንም ጓደኞች በአንዳንድ አጋጣሚ በአካል የማቃቸው ሁሉ ይቀየሙኛል በርግጥ ወግ አጥባቂ ነኝ ማለት የማወራበት አወራር ይሁን ወይም ደሞ አለመፍጠን አላቅም የሆነ ሰአት ላይ የተዋወኮቸው ቆንጆ እንደሆንኩ ይነግሩኛል እናወራለን ምናምን ከዛ እንገናኝ ካሉኝ መጀመሪያ በዚህ በደምብ እንተዋወቅ ስላቸው እየደበራቸው ይመጣል እኔ የፍቅር ጓደኛ ለመያዝ ሳይሆን ለማወቅ ፈልጌ ነው ማለት ምናልባት ከሰው ብዙ ጊዜ አልቀላቀልም እሱ ነገር ከአለም አግሎኝ ይሆን ብዬ ስላሰብኩ ነው ለትምህርት ብቻ ነው ከቤት የምወጣው ከዛ ክላስ ኮሌጅ ነኝ ቀጥታ እንዳለቀ ወደቤት ነኝ ሰርግ ለቀሶ ምርቃት ምናምን ከተፈጠርኩ ሄጄ አላቅም እና ምናልባት ያ ይሆን ከሰው ጋ እንዳልግባባ ያደርገኝ ? ለምትሰጡኝ ምክርና አስተያየት ከወዲሁ ላመሰግን እወዳለሁ 🙏
Aug 05, 2021ተግባቢ እና ተናጋሪ ለመሆን ምርጥ 5 መንገዶች | Inspire Ethiopia