ይሄ የትላንት የዋዜማ ዜና ነው። አንድ የአሜሪካ ዶላር በአዲስ አበባ ጥቁር ገበያ 65 የኢትዮጵያ ብር እየተመነዘረ መሆኑን ዋዜማ ባደረገችው ቅኝት ተረድታለች። በባንኮች አንድ የአሜሪካ ዶላር የሚገዛበት ዋጋ ከጥቁር ገበያው ምንዛሬ ጋር ያለው ልዩነት 20 ብር ሆኗል። ሰምኞ ዕለት ንግድ ባንኮች አንድ ዶላርን በ44 ብር ከ36 ሳንቲም የገዙ ሲሆን፣ ጥቁር ገበያው ግን በ65 ብር ሲገዛ ውሏል። በዛ ያለ ዶላር ለሚያቀርቡ ደንበኞች ደሞ ከጥቁር ገበያው ከ65 ብር በላይ እያገኙ እንደሆነ ዋዜማ አረጋግጣለች። በመደበኛው እና በሕገወጡ የምንዛሪ ገበያ መካከል ይህን ያህል ሰፊ ልዩነት ሲታይ ያሁኑ የመጀመሪያው ነው።
Aug 05, 2021