ሴት ነኝ እና ከዕድሜዬ በላይ ወፈር ያልኩ ነኝ ከጊዜ በኃላ የመጣ ውፍረት ነው እናም ጓደኞቼ ዘመዶቼም ባዩኝ ቁጥር ምንድነው እናት አክለሻል ወፍረሻል ይሉኛል እኔ ደግሞ ለመክሳት ብዙ ሞክሬ አልተሳካልኝም😒 እንደዛ ሲሉኝ ደግሞ ቶሎ ይከፋኛል እና ምን ይሻለኛል በማንነቴ በውረቴ confidence እንዴት ሊኖረኝ ይችላል??
Jul 30, 2021ውፍረቱ ተፈጥሮዓዊ ከሆነ (ከቤተሰብ ከሆነ) ያው የግድ የሰውነት እንቅስቃሴ መጀመር ጥሩ ነው።ከዎክ መጀመር ይቻላል(በሳምንት ሁለቴ ለ 30 min ነው የሚመከረው ግን ፈጠን ላለ ለውጥ 1 ሰዓት ፈጠን ያለ ዎክ ማድረግ፥ያው ድካም ሊኖረው ስለሚችል ከትንሽ ደቂቃዎች መጀመር ይቻላል ።ከምግብ በፊት ውሃ መጠጣት ሆዳችን ምግብ ያለው ስለሚመስለው ትንሽ ምግብ እንድንበላ ያደርገናል።ጣፋጭ ምግቦችን መቀንስ(ስኳር ያላቸው) በነሱ ፋንታ የተፈጥሮ ማጣፈጫ(ማር) ፡ፍራፍሬን መመገብ።ቴምር ትንሽ በልተሽው የጥጋብ ስሜትን ያመጣል እሱም ጥሩ ነው(የቴምር ብስኩቶች)።ቀይ ስጋን መጠቀም፥ጮማን መቀነስ።አረንጓዴ ሻይም አንድ የመክሻ መንገድ ነው።እርድ፥ስፒናች ኮልስትሮል በማቃጠል ይታወቃሉ እነሱንም ማካተት ነው።ከምንም በላይ ግን ጤነኛ ከሆንሽ ሰው አውርቶ ይደክመዋልና ያለሽንም ሰውነት መጠበቅ ይቻላል።👍
Aug 01, 2021