ኖረን ኖረን የምንሞት ከሆነ አፈር የምንሆን ባዶ የምንሆን ከሆነ ለማን ብለን እንለፉለን ለማንስ ብለን እንደዚ እንሆናለን ለመደሰት ነው እንዳትሉኝ ሰው ሁሉ እንደውጪው አደለም ሁሉም ሰው ውስጥ ባዶነት አለ ስኬታማ ሆነን ዞር ብለን ራሳችንን ስናይ ከአሁንም ባዶ ነን የምትፈልጊውን ልብስ ጫማ ቤት መኪና ገዝተሽ ግን አሁንም ባዶ ነሽ? የአለማች ምዑር ሰው ተብለህ በአደባባይ ተጨብጭቦልህ አሁንም ባዶነት አለ ግራ ትጋባለህ ቆይ እንዴት እንኑር ምድር ለይ ሌላ አማራጭ አለ ወይ ከባዶነት ሌለ?
Jul 28, 2021የመኖር አላማ እንደ ኗሪው ይወሰናል አዎ ሁላችንም ሟች ነን ግን ለመኖር መስራት መልፋት አለብን ደሞስ ባንሰራ እያንዳንዳችን አሁን ካለን ጎደሎነት የበለጠ ባዶ እንሆናለን እንጂ ከሰማይ መና አይወርድ ህይወት ላንዱ ጥሩ ትርጓሜ ላንዱ ትርጉም አልባ ናት ምክንያቱም ሁሉም በራሱ እይታ ውስጥ ነው የሚኖረው የሰው ልጅ ፍላጎት እስከ እለተ ሞቱ ስለማያልቅ ሙሉ ነኝ አይልም ደሞስ የህይወት ሙሉነት በምን መስፈርት ይለካል ብለህ ነው
Jul 29, 2021