የብሉይ ኪዳን ታቦት ለሙሴ አምላካችን እግዚአብሔር አስርቱ ትዕዛዛትን ጽፎ የሰጠበት ነው።ይህም በእግዚአብሔር ጣቶች የተጻፈም እንደመኾኑ እጅግ ክቡር ነው። የአዲስ ኪዳን ታቦት ቤተክርስቲያናችን የቃልኪዳኑ ታቦት/ጽላት/መሠዊያ የሚባል ሲኾን በቅርፅ፣በአገልግሎትም ኾነ በክብር ከብሉይ ኪዳኑ ታቦት የተለየ ነው። የብሉይ ኪዳኑ ታቦት ፲ቱን ትእዛዛት ሲይዝ የአዲስ ኪዳኑ ደግሞ "አልፋና ኦሜጋ" የሚለው የኢየሱስ ክርስቶስ ስም እና "በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ"(ፊልጵ. 2፡10)የሚል ነው(በግእዝ)፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ባልሳሳት በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የክርስቶስን ሥጋ እና ደም ለመፈተት በመሰዊያነት ያገለግላል። ታቦቱን እንደ መሠዊያነት መጠቀሙ በብሉይ የበግና የፍየል ደም ይሠዋ በነበረበት የኦሪት ዘመን እንኳን ለብቻው ትልቅ መሠዊያ ተዘጋጅቶ ፣ መሠዊያው ተቀድሶ ሰው በማይገባበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በክብር ተቀምጦ ነበር፡፡ የአማናዊው የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ እና ደም ደግሞ ከዚህ ፍፁም የላቀ እንደመኾኑ በታቦቱ ላይ ይሰዋል።...🤗❤️ ይህንን ያህል ነው የማውቀው እኔ🙏
Jul 21, 2021