ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተከታዮች ብቻ ሰላም 😊 እንዴት ናችሁ? የሆነ ጥያቄ ለመጠበቅ ፈልጌ ነበር። ጥያቄውም: በዓለማዊ ሕይወት ስንኖር የቀን በቀን ውሎአችን አምላካችን እግዚአብሔር በፃፈው ነው ወይም እሱ በፈቀደው ነው? ለምሣሌ ይህንን ጥያቄ ስፅፍ በራሴ ሳይሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው የፃፍኩት ማለት ነው? መልሳችሁ አዎ ከሆነ፣ ኀጢአት ስንሰራም እኛ አይደለንም ግን የተፃፈልን ነው ማለት ነው? ሲዖል ብንገባስ የተፃፈልን ነው ማለት ነው? 😊 ለምትመልሱልኝ ሁሉ ጌታ ያክብርልኝ። 💚💛❤️
Jul 20, 2021የአምላክነት ባህርይ ስለሆነ እግዚአብሔር አምላክ ገና አለምን ሳይፈጥራት አንቺ ምን እንደምታደርጊ ያውቃል፨ግን የምታደርጊውን ነገር ሚያስደርግሽ እሱ አይደለም ላንቺ እሳትና ውሃ ነው ሚቀርብልሽ መምረጥ ያንቺ ፋንታ ነው ምን እንደምትመርጪ ቢያቅም ግን እድሉን ከመስጠት ወደኋላ አይልም። ከሰው አይምሮ በላይ የሆነ ቸርነቱም በዚ ይታያል። አበው ምን ይላሉ መሰለሽ "አንድ ፈጣሪ ነው ተብሎ የሚታሰብ ነገር በፍጡር ከተመረመረ ያ ነገር ፈጣሪ አይደለም።" ልክ ናቸው ምክንያቱም ሁሉንም ባህሪውን ካወቅሽ ከመረመርሽው ፈጣሪነቱ ወይም አምላክነቱ ምን ላይ ነው......እዚ ላይ ምን ሃሳብ አለህ/ሽ ተጨማሪ @joelwatt
Jul 20, 2021