Hi beteseb Abzagnaw sew zefen haxiyat endehone eyaweku lemndnw gn mizefnut or miyadamxut😕🤔🤔
Jul 19, 2021Yaw sw lazi alem desita bicha silaminor nwa
Jul 20, 2021Hi beteseb Abzagnaw sew zefen haxiyat endehone eyaweku lemndnw gn mizefnut or miyadamxut😕🤔🤔
Jul 19, 2021Yaw sw lazi alem desita bicha silaminor nwa
Jul 20, 2021ደካሞች ስለሆንን ነዋ::
Jul 20, 2021Hatyat endhone eyake sw zefn yemismaw endmimslgn kenfsu belayi segawn masdest merchaw selhone yimslgnal
Jul 20, 2021የእለቱ ቁምነገር ዘፈን ሐጢያት ነው? ወይስ አይደለም? ========================= ክፍል - 1 """"""""""""" ዛሬ Tsegaw Mamo የሚባል የ book for all አባል ‹‹ዘፈን ሐጢያት ነው? ወይስ አይደለም?›› የሚል ፅሁፍ በዚህ ገፅ ፅፎ አየን፡፡ እኛም ጥቂት ለማለት ወደድን፡፡ የውዝግቡ መነሻ የአማርኛው መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ጳውሎስ በገላትያ 5፡21 ላይ ‹‹ዘፋኝ መንግስተ ሰማያትን አያስወርስም›› ማለቱ ነው፡፡ ጳውሎስ መልዕክቱን የፃፈው በግሪከኛና ለግሪክ ሰዎች ነው፡፡ የገላትያ መልዕክት ደግሞ ለገላትያ ሰዎች የተፃፈ ነው፡፡ ከዚህ እውነታ ጋር አያይዘን ሁለት ነገሮችን እናንሳ፡፡ """""" * የመጀመሪያው፣ በአማርኛ መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ‹‹ዘፈን›› ተብላ የተተረጎመችው ቃል ጳውሎስ በግሪክኛው ምን ብሎ የፃፋትን ነው? መልሱ ቀላል ነው፤ ጳውሎስ በግሪክኛ ‹‹Komos›› በማለት የፃፋትን ቃል ነው በአማርኛ ‹‹ዘፈን›› ተብላ የተተረጎመችው፡፡ """"" * ሁለተኛው ሐሳብ ከባህል አውድ (Cultural Context) ጋር የተያያዘ ነው፤ ለመሆኑ፣ ጳውሎስ በገላትያ ሰዎች ላይ ምን ዓይነት ልማድ (ባህል) አይቶ ነው ‹‹‹‹Komos›› ሐጢያት ነው›› ያላቸው? ይሄንን ጥያቄ ለመመለስ ጳውሎስ በነበረበት ዘመን ገላትያውያን ስለነበራቸው ባህል ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ """" የጥንት ግሪካውያን አማልክትና ባህል ========================= በሆሜር (ቅድመ ሶቅራጠስ) ዘመን ግሪኮች በርካታ አማልክቶች አሏቸው፡፡ ሁሉም ግሪካውያን ታዲያ ሁሉንም አማልክት እኩል አያመልኩም፤ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተለያዩ አማልክቶችን መርጠው ያመልካሉ፡፡ ከእነዚህ አማልክቶች መካከል በኒቸ ፍልስፍና ውስጥ ትኩረትን የሳቡ ሁለት አማልክቶች አሉ ― ‹‹አፖሎ›› እና ‹‹ዲዮኒሰስ›› (Apollo and Dionysus) የሚባሉ፡፡ አፖሎ ብርሃን እና ምክንያታዊነትን ለዓለም ያመጣ የፀሐይ አምላክ ሲሆን፣ ዳዮኒሰስ ደግሞ የወይን (የፌሽታ) አምላክ ነው፡፡ """"" እነዚህ ሁለት አማልክቶች የሚወክሉት ሁለት ነገሮችን ነው፡፡ ዲዮኒሰስ የሚባለው የሚወክለው ገደብ የለሽ ፍላጎት ያለውን ዓለም ነው፡፡ የፈለገውን ነገር በፈለገው ጊዜ የሚያደርግ፣ ምንም ዓይነት ገደብ የሌለው ነፃነትን ነው፡፡ ዳዮኒሰስን በአብዛኛው የሚመለከው በግሪካውያን መሳፍንቶች ዘንድ ነው፡፡ ዳዮኒሰስን የሚያመልኩ ሰዎች የሚታወቁት በምሽት እንደፈለጉ ጠጥቶ በመስከር፣ በራቁት ዳንስ፣ መንገድ ላይ በመዝፈንና በመጮህ፣ በአደባባይ ራቁታቸውን በመሄድና ወሲብ በመፈፀም ነው፡፡ ይሄንንም የሚፈፅሙት ሁልጊዜ ሳይሆን፣ የወይን ምርት በሚደርስበት ወቅት ለአምላካቸው ለዳዮኒሰስ ደስታቸውን ሲገልፁ ነው፡፡ ይሄም ‹‹የወይን ፌሽታ›› በዓል ‹‹Komos›› ይባላል፡፡ ባጭሩ፣ ‹‹Komos›› የግሪካውያን ‹‹የምሽት ፓርቲ›› በዓል ነው፡፡ በኋላ ላይ ግን ‹‹Komos›› ከማዝናናቱ ይልቅ ህብረተሰባዊ ጉዳቱ በማየሉ የተነሳ ሮማውያን በህግ አግደውታል፡፡ """""" በመሆኑም፣ ጳውሎስ ቃል በቃል ‹‹ዘፈን›› የሚለውን ቃል ፅፎ ሐጢያት ነው አላለም፡፡ ጳውሎስ ያለው ‹‹‹‹Komos›› ሐጢያት ነው›› ነው ያለው፡፡ አሁን ትልቁ ችግር የሚመጣው ጳውሎስ ‹Komos›› ብሎ የፃፈው ቃል በአማርኛ ሲተረጎም ነው፡፡ ባህልን የተሸከመ ቃል ወደ ሌላ ቋንቋ ሲተረጎም አቻ የሆነ የባህል አውድ ካልተገኘለት የፀሐፊውን መልዕክት ይስታል፡፡ ‹Komos››ን እንግሊዞች ቢጨንቃቸው እንደምንም በማቀራረብ ‹‹Orgy›› ብለው ተረጎሙት፤ ይሄም ሆኖ ግን ‹‹Orgy›› ከ‹Komos›› ጋር አይስተካከልም፡፡ በሀገራችን ከገላትያኑ ‹Komos›› ባህል ጋር የሚስተካከል ባህል የለንም፡፡ እና በአማርኛ ምን ተብሎ ይተርጎም? """"" የአማርኛውን መፅሐፍ ቅዱስ የተረጎሙ ሰዎች ለ‹Komos›› አቻ የሆነ ኢትዮጵያዊ የባህል አውድ ሲያጡ፣ በሀገራችን ከጥንት ጀምሮ ንቀትንና ውርደትን ስትሸከም የኖረችው ሙዚቃ ላይ አሸከሟት!! ምስኪን ሙዚቃ!! በሀገራችን የሙዚቃ ሙያ ላይ የተሰራው ግፍ ኢፍትሐዊና በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ እውነት ለመናገር፣ ‹Komos››ን ‹‹ዘፈን ወይም ሙዚቃ›› ብሎ ከመተረጎም ይልቅ ‹‹የምሽት ክበብ›› ተብሎ ቢተረጎም የአውድ ተቀራራቢነት አለው፡፡ እንግዲህ፣ በዚህ መልኩ ‹‹ሙዚቃ›› ላይ የተሰራው ግፍ ነው ይሄው እስከ አሁን ዘመን ድረስ ኢትዮጵያውያንን እያወዛገበ ያለው፡፡ ፀሀፊ: ብሩህ አለምነህ (የፍልስፍና መምህር)
Jul 20, 2021በመጀመሪያ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ ያለ ቃል ቃል እንደሆነ ነው የሚፀናው "ሰማይና ምድር ያልፋል ቃሌ ግን አያልፍም ነው " ነው ያለው እስላም ወንድምና እህቶቼ የእናንተንም አካፍሉን ዝም አትበሉ። ወደራሴ ስመለስ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ " ዘፋኝ መንግስተ ሰማያት አይወርስም " ተብሏል አዎ አይወርስም ግን የትኛው ዘፋኝ ከሰሊጥ ጋር የተገኘህ ኑግ አብረህ ተወቀጥ ነው ነገሩ ስለ ዝሙት የሚዘፍን ዘፋኝ እና ስለ ሰላም የሚዘፍን እኩል ሚዛን ላይ ዘፋኝ ተብሎ ነው ሚፈረድባቸው ኪዩ ስለ መጥምቁ ዮሀንስ ስትነግረን አንገቱ የተቀላው ለሰው አልዘፍንም ስላለ ነው። ስለ ሰላም የሚዘፍንስ ስለ ፍቅር የሚያጎራጎርስ
Jul 20, 2021I don't understand how is zefen haxiyat of course አንዳንድ ዘፈኖች ስለ ፍቅር እና ሴቲች ምናምን ባለጌ ናቸው ግን አንዳንድ ዘፈኖች ደሞ ኛን የእለት ተእለት ኑሮ የሚገልፁ አለ ማለት እኛ አንዳንዴ ምናወራውን እነሱ ትንሽ ምት እና ዜማ ጨምረው ስለ ተናገርሩ automatically ሀጥያት ነው ማለት አይከብድም?? ለምሳሌ የሀገር ፍቅር ዘፎኖች ከውጫገር ደሞ የ friendship፣ ምናምን
Jul 20, 20214
Jul 20, 2021Becoz they can't resist it
Jul 20, 2021Yaw genzeb masaded new nisha nege engebalen eyalu
Jul 20, 2021Asbachehutal ahun rophnan beza zefenu siol sigeba 😂
Jul 20, 2021ለእኔ የማዳምጣቸው ዘፈኖች ሀጥያቴ አይደሉም
Jul 20, 2021149
Jul 20, 2021ሁሉም ዘፈን ሀጥያት አደለም የዘፈኑን ሀጥያትነት ዘፈኑ ሊያስተላልፍ በፈለገው ሀሳብ ላይ ነው ሚወሰነው ስለዚህ መርጦ ጥሩ ጥሩውን ማዳመጥ ነው
Jul 20, 2021