Any one esti ke mekele university yemeta kale please tell me about the condition there i have a friend there and am worried so tebaberugn
Jul 18, 2021የበዛሬው ዕለት ሐምሌ 11 2013 ዓም የመቐለ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎችን ለመሸኘት የተደረገ ሙከራ በፌደራል እምቢተኝነት ከሸፈ። =============================== መቐለ ዩንቨርሲቲ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት የዩንቨርሲቲው ተማሪዎችን ለመሸኘት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ታጅቦ ምላዛት ከተማ ድረስ የተጓዘ ቢሆንም ተማሪዎቹ በዓፋር ልዩ ሃይል እንዲመለሱ ተደርገዋል። ተማሪዎቹ በፀጥታ ሃይሎች እንዲመለሱ የታዘዙት የፌደራል መንግስት ከመቐለ ዩንቨርሲቲ ጋር በገባው ስምምነት መሰረት ተማሪዎቹን ለመቀበል በስፍራው ባለመገኘቱ ነው። አንዳንድ ተማሪዎች ምላዛት እንደገቡ ለቤተሰቦቻቸው የስልክ ጥሪ በማድረጋቸው ምክንያት ቤተሰብ በልጆቻቸው መጥፋት እንዳይጨነቁ ሲል መቐለ ዩንቨርሲቲ ለድምፂ ወያነ በላከው መልእክት አሳስቧል። መቐለ ዩንቨርሲቲ የ2014 ዓ/ም በጀት እስካሁን ድረስ ባለማግኘቱ ለተማሪዎቹ የምግብ አገልግሎት ለማቅረብ ከህብረተሰቡ የዕለት ጉርሻ እያውጣጣ እንደሆነ አስታውቋል። የሰኔ ወር 2013 በጀትም አልደረሰኝም ያለው ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹን ሙሉ ሃላፊነት ወስዶ ተገቢ እንክብካቤ እያደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል። በትግራይ ሁሉም ዓይነት ግንኙነቶች ሙሉ በሙሉ በፋሺሽት አብይ በሚመራው ፌደራል መንግስት የተቋረጡ ሲሆን ተማሪዎቹም ደህንነታቸው ተጠብቆ አስፈላጊዉን ሁሉ አገልግሎት እያገኙ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። #DW It's #Tigray we value ppl
Jul 19, 2021