ስለም ለሁላችሁም ስለ ኦርቶዶክስ አፅዋማት እና እስከ ስንት ሰዓት እንደሚጾም ማወቅ እፈልጋለሁ አክፍሎት ምን እንደሆነ? ፫ ቀን ነው ምፆመው መቅደስ ለመግባት ማሕሌት ለመቆም? እንዴት እንደሚጾም? እናም ጋድ ምንድን ነው? ጋድ ሚደረገው መች ነው? ፀሎተ ሐሙስ ላይ ለመቁረብ መች እና እስከ ስንት ሰዓት ነው ምፆመው? ስለ ጳጉሜ ጾም ምታውቁት ካለ? አመሰግናለሁ
Jul 16, 2021#አክፍሎት ምንድነው?ታሪካዊው_ዳራዉስ? 👉በሰሙነ ሕማማት ዕለተ አርብ ከስግደት በኋላ ምዕመናን በየቤታቸው ጥቂት ነገር ቀምሰው እስከ እሁድ /የትንሳኤ ሰዓት/ ይሰነብታሉ፡፡ ይህ አክፍሎት ይባላል፡፡ ብዙው ምዕመን ከዓርብ ጀምሮ የሚያከፍል ሲሆን አንዳንዶች ግን ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ፡፡ 👉ይህም እመቤታችን፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ የጌታን ትንሣኤ ሳናይ እህል ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሣኤ መቆየታቸውን ተከትሎ የመጣ ትውፊት ነው፡፡ 👉ይህንን ትውፊት አስመልክቶ ሄሬኔዎስ፣ አውሳብዮስ የተባሉ ጸሐፍት፤ ሐዋርያት በሰሙነ ሕማማት ከደረቅ ዳቦ አና ከትንሽ ውኃ በቀር እንደማይመገቡ እና ከሐሙስ ጀምረው እንደሚያከፍሉ ጽፈዋል፡፡ 👉ይህም ብቻ ሳይሆን ሐዋርያት ሌሎቹንም እንዲያከፍሉ እንዳሳሰቡና ከሐሙስ ጀምሮ ያልተቻለው ቢያንስ ከዓርብ ጀምሮ እንዲያከፍል ማዘዛቸውን ጽፈዋል፡፡ 👉እኛ ቤተ ክርስቲያን ትምህርትም ይኸው ነው፡፡ ቅዳሜ ይበላል ማለት ግን ቅዳሴው ሌሊት ስለሆነ በልቶ ማስቀደስ ነውና በልቶ እንደመቁረብ ይቆጠራል፡፡ @orthodoxmeme1 or @orthodoxmeme2 @abel0606
Jul 17, 2021