ብትወደኝማ ኖሮ… ቀኑም አይመሽልኝ ጊዜውም ፈቅ አይል የአጥሩን መነሳት እያወኩ ዝም አልል ምሰክር ይምስለኛል በደስታ ምነከር ምጨበጠው ጠፍቶ በሰማይ የምበር የታፈነው ስሜት ፈንፍሎ በድንገት ሚሆነውን ፈራው እንዳሰራ ስህተት አንተን ላለማጣት ስጎዳ ኖርያለው በጓደኝነት ስም ብዙ ከፍያለው ታቅልኝ ነበር ግን… ባታቅም ግድ የለም ለራሴ ነው ትርፉ እኔው ፈልጌው ነው ሳታውቅ ማለፉ ስለ እሷ ስትነግረኝ ስለ ፍቅርህ ግዝፈት የመውደድህን ጥግ ስትገልጽ በምስጠት በደስታህ መደሰት ልምድ ባይሆንብኝ በምን ሀይል ችዬው አቅምም አላገኝ ፍቅረኛ የያዝክ ቀን እንቅልፍ ባይኔ ሳይዞር ከሀውልት ደርቄ አስጠልቶኝ መኖር ሀዘንና ጸጸት በአንድነት ሲጥሉኝ መቁቋም አቅቶኝ መራቁን ወሰንኩኝ ታውቅልኝ ነበር ግን… ከዛም ስትናፍቀኝ ማፍቀር መስፈርት የለው ብዬ ተመለስኩኝ አፍቃሪ እውር ነው ብትወደኝማ ብዬ አስባለው በጥልቅ ከእውነታው ሽሽት እሄዳለው ሩቅ የኔ ሆነህ ማለም አንተን የማየት ህልም የማትቀረው አንተ የማልተውህ ፍፁም ፍቅሩንስ እችላለው ማልችለው ሀዘንህ ማልችለው እንባህን ማልችለው ጭንቀትህ በድህና ቆይልኝ እንደው ለኔ ብለህ የሀሳብህ ተካፋይ የልብ ጓደኛህ ነኝ አላሳፍርህም አልክድም አምነኸኝ አፍቃሪ ጓደኛህ😔 ሰዎች በጣም እየተጎዳው ነዉ ምን ተሻለኝ? ጕደኛዬን መራቅም መቅረብ አልቻልኩም ምን ላርግ?
8 votes