Hey gayes e...mn miselachu and mewdat metodegh lij nibrech ena haymanotachen gn yeteleyaye nw ena mn aynet wesana mewsin alebigh?
Jul 12, 2021ከፍቅረኛዬ ጋር የተለያየ ኃይማኖት እንዳለን ሳውቅ ግንኑነቱን አቆምኩኝ፣ እሷ ግን አልተዋጠላትም፣ ምን ላድርግ? ጥየቄ፡- ዶክተር እንዴት አመሸክ? በመጀመሪያ ስለምታደርገው ነገር እግዚአብሄር ውለታህን ይክፈልክ፡፡ በመቀጠል ዶክተር አንድ ጥያቄ ነበረኝ:- ከአንዲት ልጅ ጋር በአጋጣሚ ተዋውቀን ነበር እናም ስልክ ተቀያይረን ማውራት ጀመርን፡፡ ሁለት እና ሶስት የሚሆን ግዜ ተገናኝተን አውርተናል ለአንድ ወር ያክል ከዚያ በአጋጣሚ ስለ እምነት ማውራት ጀምረን፡፡ የተለያየ እምነት ተከታዮች ነን፡፡ ይሄን ስሰማ ጓደኝነቱን አቆምኩኝ፣ ለሱዋም ነገርኩዋት ግን ልትረዳኝ አልቻለችም፡፡ መጀመሪያ ሠሞን ሀሳቤን ነግሬአት ተማምነን ነበር ግን ልጅቷ ስልክ መደወሉን አላቆምም አለች፡፡ እኔ በህትነት ነው የማወራት አናም በተደጋጋሚ በመደወል ስታጨናንቀኝ ስልኳን ብሎክ አደረኩት፡፡ አሁን ሳላገኛት ስድስት ወር አልፎኛል እሷ ግን ጭራሽ እየባሰባት ነው፡፡ ያልኳትን ሁሉ ረስታ አብረን መሆን አለብን ትላለች፡፡ እኔ ደግሞ ከዛሬው ይልቅ ነገ ከባድ ነው፣ የተለያየ እምነት ሆነን አብረን አንቀጥልም የሚል እምነት ነው ያለኝ፡፡ እና ዶክተር ምን ላድርግ? ምክንያቱም ዶክተር በኔ እምነት ነገ ላይ አንድ ላይ እየኖሩ በእምነት ጉዳይ አለመግባባት መፈጠሩ አይቀሬ ነው ለዛም ነው ብዙ ሳንሄድ ማስቆም የፈለኩት፡፡ መልስ፡- ያነሳኸው ጉዳይ በፍቅረኞች መካከል ሊኖሩ ከሚገባቸው የመመጣጠን ሁኔታዎች አንዱን ነው ይኸውም “መንፈሳዊ (የእምነት) መመጣጠን”፡፡ በቅር ባሳተምኩት መጽሐፍ ውስጥ ይህንን ሃሳብ አስመልክቶ የሰጠሁትን ማብራሪያ ላስፍርልህና በዚያ መሰረት ውሳኔህን ወሰን፡፡ ማስታወሻ፡- ለወጣቶች በመመጣጠን ጉዳይ ላይ ትምህርት ስሰጥ ከሚነሱ ጥያቄዎች አንዱ “መመጣጠን” በሚለው ሃሳብ ውስጥ “መንፈሳዊ” ዘርፍ እንዴት ይታያል የሚል ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በርካታ ሰዎች የሚያነሱት ጥያቄ ነው፡፡ በተለይም እንደእኛው አይነት የተለያዩ አንጋፋ ኃይማኖቶች በአንድነትና በመዋደድ በሚኖሩባት ሃገር ውስጥ ሊነሳ የሚገባው ሃሳብ ነው፡፡ የጥያቄው መነሻ፣ “አንድ ሰው በመንፈሳዊ እምነቱ ወይም በኃይማኖቱ የሚመጥነውን ሰው ማግባት የለበትም ወይ?” የሚል ነው፡፡ የዚህ ጥያቄ ወሳኝነትና ተግባራዊነት ሊካድ አይቻልም፡፡ “መንፈሳዊ መመጣጠንን” አስመልክተን ስንነጋገር አንዱ ያለን አማራጭ በዚህ የአመለካከት መመጣጠን ዘርፍ ውስጥ አዳብሎ ማየት ሲሆን፣ ሌላው አማራጫችን ግን የመንፈሳዊ መመጣጠንን ዘርፍ ለብቻው ማስተናገድ ነው፡፡ እዚህም ጨመርነው እዚያ፣ ዋናው ቁም ነገር ይህንን ለበርካታ ትዳሮች የውጥረት ምክንያት ሊሆን የሚችለውን ያለመመጣጠን ጉዳይ እንዴት ልናየው ይገባል የሚለው ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ በጉዳዩ ላይ ንቃተ-ህሊና ከመፍጠር ባሻገር ብዙ ትንታኔ የመስጠትና በሰፊው የመዘርዘር ዓላማ ባይኖረኝም የተለያየ እምነት ያላቸው ሰዎች ወደ ፍቅር ሕይወት ሲገቡ በጉዳዩ በሚገባ ሊያስቡበት እንደሚገባ ልናሰምርበት ይገባል፡፡ ስለሆነም፣ ማንኛውም ወንድ ወይም ሴት ከእምነታቸው ተቃራኒ እምነት ያለውን ተቃራኒ ጾታ ለፍቅር በሚያስቡበት ጊዜ ልዩነቱ ይዞ የሚመጣውን ሁኔታ በሚገባ ማጤን አስፈላጊ ነው፡፡ ከእምነት ልዩነት የሚመጡ ውጥረቶች ቁጥራቸው ብዙ ነው፡፡ አንዳንዶቹ የልዩነት ውጥረቶች ገና የፍቅር ጉዞው “አሃዱ” ተብሎ ሲጀመር አብረው የሚወለዱ ሲሆኑ፣ ሌሎቹ ደግሞ ቀስ በቀስ ብቅ እያሉ በመግባት ግንኙነትን የሚረብሹ ናቸው፡፡ በፍቅር ጅማሬ ወቅት በእምነታቸው የተለያዩ ሰዎች የፍቅርን ጎዳና ሲጀምሩ ምንም እንኳ በጉዳዩ አምነውና እርስ በርስ ተማምነው ቢጀምሩም ከሁለቱም ወይም ከአንዱ ወገን የሚመጣ የቤተሰብ ሃሳብና ጣልቃ-ገብነት ካለመመጣጠን የሚመጣውን ውጥረት አንድ ብሎ ያስጀምራቸዋል፡፡ ብዙ ወጣቶች ካላቸው ፍቅር የተነሳ ይህንን ውጥረት ቢያልፉትም በወቅቱ የተነሳውን የውዝግብ ዘር ይዘው ወደትዳር ስለሚገቡ ጉዳዩ እንደገና የማገርሸቱን አደጋ እንደተጋፈጡ ይኖራሉ፡፡
Jul 13, 2021