ወንድ-22: እናቴ ብቻዋን ነው ያሳደገችኝ ብቸኛ ልጇ ነኝ አብዛኛውን የልጅነት ጊዜዬን ከቤት ሰራተኛ ጋር ነው ያሳለፍኩት እናቴ አብዛኛውን ጊዜ ካጠገቤ አልነበረችም ስራዋ ላይ በቻ ነበር ምታተኩረው ፡ አባቴን በቅርብ ነው ያገኘሁት ከእናቴ ጋር ያለኝ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበላሸ ነው በቃ በሆነው ባልሆነው ነው ምንጨቃጨቀው እያንዳንዱ ድርጊቴ ያናዳታል፡ እናትና ልጅ ሁላ አንመስልም ለእናቴ እንደማንኛውም ልጅ ፍቅር አለኝ ግን ያንን ማሳየት ያቅተኛል ለመጨረሻ ጊዜ ያቀፍኳት ጊዜ ራሱ አላስታውስም፡ አሁን ነገሮች ከቁጥጥር ወጭ ሳይሆኑ እንዴት ማስተካከል እነዳለብኝ ጨነቆኛል እርዱኝ እባካቹ
Jul 11, 2021እንደዚ የምትሆነው በሰው ግፊት ከሆነ ተውውውዎ የምር እናትህ ናት መተኪያ የሌላት አታስከፋት ላንተ ያረገችውን አስታውስ ለዚህ መድረስህ ከፈጣሪ በታች እናቱን ታድሎ የሚያስደስተው ከስንት አንድ ነው እድሉ አያምልጥህ ጥሩ ልጅ ሁንላት ብትናረርህም አንገትህን ደፍተህ ዝም በል ታዘዛት
Jul 11, 2021