Hey everyone✋ What's the best advice anyone has given to you or best lesson life has thought you?
Jul 08, 2021Most of life consulting advises are from my father. They are a lot but some of them are.. "የኔ መኖር ባንተ ውስጥ ነው። የኔ ስኬት፥ ያንተን ስኬት ማየት ነው። እኔ ያለፍኩበትን መንገድ አንተም መጓዝህ አይቀርምና፥ ደጋግሜ አንተን እንዲህ የምመክርህበት ምክንያት፤ እኔ የሠራኋቸውን ስህተቶች አንተ እንድትደግመው ስለማልፈልግ ነው" ❝ዓላማህን የምታሳካበት የመጀመሪያ ሥራህ መማር ነው። ሥራህን ለነገ አትቆጥብ። ሰነፍ ማለት ብሩህ አእምሮ የሌለው ሳይሆን፤ ሥራውን፥ ነገን ለሚወልደው ነገ እየቆጠበ ብሩህ አእምሮውን በሜዳ የበተነ ሰው ነው። ስለዚህ ነው አትስነፍ ብዬ የምነግርህ❞ ❝ያንተ ሃሳብ ምንም ይሁን ምንም፥ የወደፊት ህይወትህን የሚያቃና፣ የህሊና እረፍት የሚሰጥህ፣ አእምሮህን ሥራ ላይ የሚያውል ይሁን እንጂ አይደለም ያለችኝን ጥቂት ነገር ላካፍልህ፥ ካስፈልገ እንደ ምንጣፍ ተዘርግቼልህ አሻግርሃለው። እኔ የምፈልገው ያንተን ከፍታ ብቻ ነው፤ እንድትጦረኝም እንድትዶግመኝም በፍጹም አልመኝም❞ And so on. Anyways, Now he is dead and his immortal advises inspirationally always rings in my mind; I was lucky. Thanks God I had a father like him❤️
Jul 09, 2021