ሰላም everyone እንዴት ናችሁ ዛሬ አንድ ነገር እንድታማክሩኝ እፈልጋለሁ የ9th ክፍል ተማሪ ነኝ እድሜየ ደግሞ 16 በጣም የምወዳት ልጅ አለች የምንማረው 1 ክላስ ነው በጣም ከምገልፀው በላይ ቆንጆ ናት እንዲሁም በትምህርትም በጣም genius ከሚባሉ ትንሽ ተማሪወች አንዷ ነች ከሷ ጋር የተዋወቅነው ከ ሁለት አመት በፊት ነው ለሷ ያለኝ ስሜት የፍቅር መሆኑን ግን የተረዳሁት በኮረና ምክንያት ትምህርት ሲዘጋ ነው የማስበው በሙሉ ስለሷ ሆነ እሷን ሳላይ መዋል አቃተኝ በቃ ስራየ ሁሉ ከሷ ጋር በተለያየ ጊዜ የተነሰናቸውን ፎቶወች መመልከት እና edit ማድረግ ሆነ ከዛ ግን ትምህርት ተከፍቶ ስንገናኝ በጣም ደስ አለኝ በአሁኑ ሰአት best friend ነን ማለት ይቻላል ግን እኔጋ ቀን በቀን ለሷ ያለኝ ፍቅር እየጨመረ ሄደ እኔጋ ያለው ስሜት እሷጋ ያለ አይመስለኝም እና እኔጋ ያለውስ ስሜት ነግሪያት ቁርጤን አውቄ እንዳልረጋጋ ከዚህ በፊት በጣም ብዙ ሰወች ጠይቀዋት በዚህ ሰአት እንደዚህ አይነት relation መጀመር እንደማትፈልግ ነግራ ትርቃቸዋለች እናም ብጠይቃት አሁን ያለንን ግንኙነት የማጣው መሰለኝ ይህ ደግሞ ለእኔ ከባድ ነው አይደለም እያየኋት ላላወራት ይቅርና ትምህርት በሌለን ጊዜ እንዴት እንደምሆን አውቀዋለሁ ሳልነግራት ዝም ብየ ስሜቴን በውስጤ ይዠ እንዳልቀመጥ ደግሞ በጣም ከበደኝ እና gays ምን ባደርግ ይሻላል please እርዱኝ 🙏🙏
Jul 05, 2021እኔን የገረመኝ በ 16 አመትህ እንደዚህ አይደለም ፈላ ቺክ የ 40 ዓመት ቺክ የሚያሰምጥ አነጋገር ማወቅህ ነው 🙃
Jul 06, 2021