Tell me all about the Virgos and what you know about Virgo people
Jul 05, 2021ከነሀሴ 17 እስከ መስከረም 12 🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱 »» በኑሮዋ ሚያጋጥሟት ጥቂት ብስጭቶች ተስፋ አያስቆርጧትም። ቪርጎ ሴት ማህበራዊ ህግ ጣሰች ሲባል ብትሰማ ጨርሶ እንዳታምን። »» አስተሳሰቧም ጥርት ያለ ነው። በፍቅር ላይም እንደዚያው ጥርት ያለ ግንዛቤ ነው ያላት፣ እውነተኛ ፍቅር ብቻ። ከዚህ ከፍ ወይም ዝቅ ያለ ጨርሶ አይስባትም። »» ተዳፍኖ ያለው የቪርጎ ፍቅር እንዴ ከፈነዳ ተራራ የሚያንቀጠቅጥና ውቅያኖስ የሚያናውጥ ነው የሚሆነው። »» ከቤተሰብ መለያየትን የማትወደውን ያህል ግብዝነትንና መመፃደቅንም ይበልጥ አጥብቃ ትጠላለች። »» የቀረባትን ፍቅር ሀቀኛ ነው ብላ አንዴ ከተቀበለች ስለግንኙነታቸው ያላት ጥርት ያለ አስተሳሰቧ ከማንኛውም በወረቀት ላይ ካለ ህግ ይበልጥ ይገዛታል። »» በዞዳይክ ውስጥ ፍፁም የተግባርና የፍቅር ሴት ቪርጎ ናት፣ ያለ እሷ በስርዓት፣ በብቃትና በጥራት የሚሰራ ማንም የለም ብላ ታምናለች። »» በርግጥ ነገሮችን በስርዓት በብቃትና በከፍተኛ ጥራት እንደሷ የሚሰራ ሌላ ሰው በመዛኙ አይገኝም። »» ወዲያው ይከናወን ይሰራ ባይም ናት። በቀጠሮ አስጠብቀሃት ታውቃለህ? በጣም ነው ምትናደደው። »» ቪርጎ ሴት ስህተቷን አምና በመቀበል ረገድ አእምሮዋ የተዘጋ ነው፣ ጨርሶ አታደርገውም። »» ከቪርጎ ሴት ጋር ቀጠሮ ካለህ ፀባይህን አሳምር፣ አነጋገርህን አለዝብ፣ አለባበስህን እስተካክል። »» ያልታረመ ፀባይ፣ ስድ አነጋገርና አልባሌ አለባበስ ይዘህ አትቅረባት አትወድም፣ አስተሳሰቧ ጥርት ያለ ስለሆነ ውዥንብር ነዝተህ ልታምታታት እንዳትሞክር፣ ታውቅብሃለች። »» እሷ እውነትና እውነት ብቻ ነው ካንተ የምትጠብቀው። ለሷ እውነት ውበት ነው፣ ውበትም እውነት ናት። »» ጥልቅ የሀላፊነት ስሜት የሚሰማት ጭምቷ፣ ጨዏዋና ጠንካራዋ ሴት በርካታ አባላት ያሉትን ትልቅ ቤተሰብ እርስ በእርሱ በፍቅር አስተሳስራ የምትይዝ ምትሀተኛ የፍቅር ገመድ ናት።😌😌
Jul 06, 2021