እውነት ለመናገር ሜካብ በጣም ነው ምጠላው ሰዎች ተቀብተው ሳይ እውነት ሳቄ ይመጣል በተጨማሪም ለነሱ አፍራለሁ ........እኔ የሚሰማኝ ሜካብ ከተቀባው ምንም አይነት confidence እንደማይኖረኝ ነው ስለዚህ መቼም ማረግ አልፈልግም እና ችግሩ ምን መሰላችሁ 2011 ላይ የአክስቴ ልጅ ሰረግ ነበርና ቤተሰብ ጫና አርጎብኝ ነበር እንድቀባ እነ በጣም ጭቆጭቅ ነበር ያው ለሰረጉ ነው ምናምን ብለውኝ ነበር ከዛ እኔም የምቀባው ከዚ ቤት የማልወጣ ከሆነ ነው ብዬ አናድጃቸዋለሁ ከዛ ትተውኝ ነበር....btw በዚ ነገር አባቴ ብቻ ይደግፈኛል ግን አሁን የእህቴ ሰረግ በቅርቡ ነው ምን እንደምል አላቅም🤔 አሁን ላይ ሜካብ ለሰው ልጅ necessary ሆኗል ይገርማል ግን በዚ ጉዳይ ላይ ምን ታስባላችሁ ሜካብ ለእናንተ አስፈላጊ ነው?
Jul 03, 2021Male here. እና በጣም ነው ሜካፕ ሴቶች ሲቀቡ የምናደደው። የውሸት ረጃጅም ጥፍሮች ፥ የውሸት ቅንድብ ፥ ፊት ላይ በጣም ብዙ ኬሚካል... እኔ የምመኘው የማገባት ሚስት በሰርጋችን ቀን ፊቷን እንደታጠበች እንድትመጣ ነው። እግዚአብሔር የሰጣትን ውበት ሁሉም እንዲያይልኝ። እንጂ የማላውቃት ፊቷ የተወጠረ ሴትየው ሆና እንድትመጣ አልፈልግም። እና ምን ልልሽ ነው አባትሽ ብቻ አይደሉም እኔም እደግፍሻለሁ፡፡ ባለሽ መልክ ኩሪ! ጀግና ነሽ! እንዳንቺ አይነት ሚስት ነው የማገባው!
Jul 03, 2021