ስላም አንድ ግራ ያጋባኝ ጥያቄ አለኝ ከዚህ በፊት በአስራ ቤቶች እድሜ ላይ እያለሁ ስለ ሀይማኖት እና እምነት ምን ግንዛቤ አልነበረኝም በዛ ጊዜ ነበር የተሳሳትኩት ከሰው አይቼ የporn video ማየት ጀመርኩ እናም ሳይ ለጊዜ የሚቆይ እንደ ደስታ አይነት ስሜት ይሰማኝ ነበር እንደ ሱስ ይመስል ተከታትዬ ማየት ጀመርኩ ሀጥያት መሆኑን ያወቅኩት ስለ ሀይማኖት መከታተል ስጀምር ነበር እናም ውስጤ በጣም ተረበሸ በፈፀምኩት ሀጥያት እራሴን ማርከሴ ታወቀኝ ምን ዋጋ አለው እኔሜ በተክሊል ምሞሸር መስሎኝ የልጅነት ነገር የወደፊት ህልሜን አጨለመው አሁን መጠየቅ ምፈልገው ይህን የግል ዝሙት በንስሀ ተመልሶ በተክሊል መጋባት ይቻላል ያው ለተክሊል ድንግልና ስለሚያስፈልግ ነው በመፅሐፍ ቅዱስ ደግሞ በፀሎተ ሀሙስ እለት እግዚአብሔር እግሩ ላይ ወድቃ በሽቶ እየቀባች ስታለቅስ የነበረች ዘማዊት ሴት ይቅር ብሉ ወደ ቀደመ ንፅህናዋ መልሶታል ታዳያ የኔስ በግለ ወሲብ ያጣሁት ክብረ ንፅህናዬ በንስሀ እጥቤ በተክሊል መሞሽር ይቻለኛል?
Jun 30, 2021ኢየሱስ መሀሪ አምላክ ነው። ነገር ግን አንቺ ወደዛ አትመለሺ እንጂ፡፡ የዮሐንስ ወንጌል 8:3 ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው። የዮሐንስ ወንጌል 8:4 መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። የዮሐንስ ወንጌል 8:5 ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት። የዮሐንስ ወንጌል 8:6 የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤ የዮሐንስ ወንጌል 8:7 መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ። ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው። የዮሐንስ ወንጌል 8:8 ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ። የዮሐንስ ወንጌል 8:9 እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች። የዮሐንስ ወንጌል 8:10 ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ። አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት። የዮሐንስ ወንጌል 8:11 እርስዋም። ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች። ኢየሱስም። እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት። ኢየሱስ ይወድሻል። I advise you more to join @SisayAzusaRevivall
Jun 30, 2021