Wassup sweethearts so the thin' is I've a debate tomorrow ena the topic is "should abortion be legal?" and I'm team yess so the problem here is I literally have no idea abt that so please drop some pts(only if ya think that it should be legal)😭Btw it's Amharic lol
Jun 30, 2021I hope this gives you some perspectives you dipshit ++ ሔሮድስ በሥራ ላይ ነው ++ በዓለማችን በቀን እስከ መቶ ሃያ አምስት ሺህ ጽንስ ማስወረድ ይደረጋል ፤ ይህም በዓመት እስከ ሃምሳ ሚልዮን ሕፃናት በውርጃ ይሞታሉ ማለት ነው፡፡ ሔሮድስ መቶ አርባ አራት ሺህ ሕፃናትን ጨፈጨፈ ፣ ሂትለርም ስድስት ሚልየን ንጹሐንን ገደለ እንላለን እንጂ በውርጃ የሚገደሉት ንጹሐን ቁጥር ግን አሁንም ሔሮድስ በሥራ ላይ ነው የሚያሰኙ ናቸው፡፡ ከሔሮድስ ሸሽተው እንዳይሰደዱ እናታቸው ለሔሮድስ ወስዳ የምትሠጣቸው ሕፃናት ብዙ ናቸው:: ወዳጄ እየነገርኩህ ያለሁት ሕይወትን አደጋ ላይ በሚጥል አስገዳጅ የጤና ችግር ምክንያት ስለሚፈጸም ውርጃ ሳይሆን እናት ወይም አባት መውለድን ስላልፈለጉ ብቻ የሚሞቱ ሕፃናት ነው፡፡ ፈጣሪ ይስማቸውና ልጅ ለመውለድ እየተመኙ በዕንባ የሚጸልዩ ፣ የመካንነት ክሊኒክ /infertility clinic/ ወረፋ ይዘው የሚጠብቁ ብዙ ምስኪኖች እንዳሉ ሁሉ በቀን ውስጥ በእናታቸው ሆድ ሳሉ ሞት የሚፈረድባቸው ብዙኃን ናቸው፡፡ ድሮ ድሮ ጽንስ ለማስወረድ ከሕግም አንጻር ምክንያት ይጠየቅ ነበር፡፡ አሁን ላይ ግን እናት ከፈለገች ለምን እንዴት የሚል ጥያቄ የሚጠይቅ ተቅዋም እንኳን የለም፡፡ እንደ አሜሪካን ባሉ ሀገራት ‘ዘጠኝ ወርስ ቢሞላው እናት ከፈለገች መብቷ ነው’ የሚሉ የመግደል መብት ተከራካሪዎች እንደ አሸን የፈሉ ሲሆን ለደሃ ሀገራትም ልጅ ለማሳደግ ከሚደረግ እርዳታና ድጋፍ ይልቅ ለጽንስ ማስወረድ የሚደረግ ድጋፍ እጅግ በእጥፍ ይበልጣል:: ከማዋለጃ ይልቅ ማስወረጃ ክሊኒኮችን የማብዛት ሥራ በጥድፊያ የሚከናወንበት ሁኔታም ላይ ደርሰናል፡፡ በእናቱ ማኅፀን ያለ ሕፃን ሰው ነው፡፡ የመኖር መብቱም በሌሎች መልካም ፈቃድ ላይ የተመሠረተ አይደለም፡፡ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ከሔድን ጽንስን መግደል ‘ከማሕፀን ጀምሮ አንተ አምላኬ ነህ’ እንዲል ፈጣሪን ማምለክ የጀመረ ሕፃንን መግደል ነው፡፡ ፅንስ ማስወረድ መጥምቁ ዮሐንስን ፣ ‘’ከማሕፀን ጀምሮ መረጥሁህ’ የተባለ ኤርምያስን መግደል ነው፡፡ በጣም የሚያሳዝነው በየትኛውም ዓለም ሕግ አንድ ሰው አንዲትን እርጉዝ ሴት ቢገድል ሁለት ሰው እንደገደለ /double homicide/ ተደርጎ ይፈረድበታል፡፡ ያረገዘችው ሴት ስታስወርደው ግን መብትዋ ነው ተብሎ ይታለፋል፡፡ በመንፈሳዊ ዓይንም ካየነው አንዲት ሴት እርጉዝ ሆና ብትሞት በዕለተ ምጽአት በሙታን መነሣት እርስዋም የጸነሰችው ልጅዋም ይነሣሉ፡፡ ‘‘ተወልደው ዓመት የሆናቸው ሕፃናት ፈጽመው ይናገራሉ ከፀነሱ ሦስት ወር አንድ ወር ሲሆናቸው የሞቱ ሴቶች ከልጆቻቸው ጋር አብረው ይነሣሉ’’ ተብሎ እንደተጻፈ፡፡ /ዕዝራ ሱቱኤል 4፡21/ አንዳንድ እናቶች ፅንሱ በአስገድዶ መድፈር የተጸነሰ እንደሆነስ ይላሉ፡፡ ወዳጄ አባት ባጠፋ ንጹሕ ልጅ መቀጣቱ ፍትሕ ነውን? ፅንሱ ‘ማስታወስ አይችልም /memory የለውም/ ፤ ራሱን አያውቅም /self awareness የለውም/ የሚሉ ተከራካሪዎች አሉ፡፡ ማስታወስ ያልቻለ መገደል አለበት? ራሱን የማያውቅስ ሞት ይገባዋል? አንድ ሰው በአደጋ ምክንያት ኮማ ውስጥ ቢገባ ራሱን አያውቅም ተብሎ ይገደላል? ራሱን እስኪያውቅ ይጠበቅ የለምን? ምስኪኑ ሕፃን ለዘጠኝ ወር ያህል ቢጠበቅ ምናለ? ፅንስ ማስወረድ እንዴት እንደሆነ በቪድዮ አየተሽ ይሆን? ውርጃ የሚካሔደው እንደ ፅንሱ ዕድገት መጠን ወደ ማሕፀን መጣጭ መሣሪያ ወይም ብረት አስገብቶ ፅንሱን በማፈራረስ ተራ በተራ እጁን እግሩን በመቆራረጥ ፣ የራስ ቅሉን በማፍረስ ነው፡፡ ከዚህ አሰቃቂ ሒደት በኋላ ሐኪሙ የተቆራረጡትን የሕፃኑን አካላት አንድ ላይ አስቀምጦ ‘ሁለት እጅ ሁለት እግር’ እያለ በመቁጠርና ድጋሚ በመገጣጠም የጎደለ እንዳይኖርና ውስጥ ቀርቶ ኢንፌክሽን ፈጥሮ እናትን እንዳይገድላት በመጥረግና በማጽዳት የሚከናወን ነው፡፡ ነገሩን ባለሙያው በሚረዳበት ልክ እናት ብትረዳ ኖሮ የልጅዋን የልብ ምት እየሰማችና ሲንቀሳቀስ እያየች እንዲሞት የምትፈርድ እናት አትኖርም ነበር፡፡
Jun 30, 2021