የአብነት ትምህርት ቤት መጀመር ፈልጌ ነበር እኔ ስለ ኦርቶዶክስ እምነት ምንም እውቀት የለኝም ማለት ይቻላል እናም አሁን ማወቅ ምፈልገው ትምህርቱ ለጀማሪ ምንም ነገር ለማያውቅ ሰው ይሰጣል? ሌላ ደግሞ ትምህርቱ ምን ምን ያካትታል? ግእዝ አብሬ ነው ምማረው? ትምህርቱ መች መች ነው ሚሰጠው? ከእኔ ሚጠበቁብኝ ነገሮች ምን ምንድን ናቸው? በትልልቅ በአላት ላይ ለመዘመር ምን ያህል ጊዜ መማር አለብኝ? በገና ወይም ከበሮ ወይም ጸናጽል ያስተምሩኛል? ሌላ ማወቅ ምፈልገው የ theology ትምህርት ለወንድ ብቻ ነው ወይስ ሴት መማር ትችላለች?
Jun 28, 2021🌿 አዎን ለጀማሪ ይሰጣል። ወንድሜ እንዳለኽ መምህሩን አናግረኽ ከፊደል ትምህርት መጀመር ትችላለኽ። 🌿 ትምህርቱ የሚያካትተው የቃል ጥናት (ውዳሴ ማርያም): የንባብ ትምህርት ( መዝሙረ ዳዊት የመሳሰሉት): የዜማ ትምህርት (ቅዳሴ): ገፋ ካልክበት ቅኔ : ዜማ ብዙ መኼድ ትችላለኽ። 🌿 ግእዝን በተለያዩ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ገብተኽ መማር ትችላለኽ : በቴሌግራምም የሚያስተምሩ ቻናሎች አሉ : መጻሕፍትም ብዙ አሉ መጠቀም ትችላለኽ። 🌿 ቀኑ እንደየመምህሩ ይወሰናል። 🌿 ካንተ የሚጠበቅብኽ ፍላጎት ብቻ ነው። 🌿 በዓላት ላይ ለመዘመር በሰንበት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ገብተኽ መማር ነው። ለአገልግሎት የምትቀጣበት ጊዜም እንደየሰንበት ትምህርት ቤቱ ነው። ግን ከአገልግሎቱ በፊት ትምህርቱን እና ሕይወቱን ብታዳብር የተሻለ ይኾናል። 🌿 በገና : መሰንቆ የመሳሰሉትን የሚያስተምሩት ኹሉም አይደሉም። እንደ ግእዙ ግን በቴሌግራም ልታገኘው ትችላለኽ። ከበሮ እና ጸናጽል ግን ታገኛለኽ። 🌿 የ theology ትምህርት ወንድም ሴትም መማር ይችላሉ። አዲስ አበባ ከኾንክ ቅድስት ሥላሴ (4 ኪሎ) : ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ዻውሎስ (ኮልፌ ልኳንዳ) አለልኽ።
Jun 28, 2021