በቤተክርስቲያን ህግ አጭር ቀሚስ መልበስ ይፈቀዳል እንዴ ? ካልተፈቀደ ማስረጃ አቅርቡልኝ ?
Jun 28, 2021በፍጹም አይፈቀድም!!! እንኳን አጭር ቀሚስ ለሴቶች ሱሪ እራሱ መልበስ አይፈቀደም!!! 📌ማስረጃ📌 “ሴት የወንድን ልብስ አትልበስ ወንድም የሴትን ልብስ አይልበስ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው፡፡” (ዘዳ. 22፡5) ማንኛዋም ሴት የሰውነቷን ቅርፅ የሚያሳይ ወይም ክፍትፍት ልብስ ለብሳ መሄዷ የሁሉንም ወንዶች ስሜት መፈታተኗ እርግጥ ከመሆኑም በላይ በመንፈሳዊ ህይወት ደካማ የሆኑትን ደግሞ ለኃጢያት አጋልጦ ይሰጣል፡፡ እዚህ ላይ የተሳሳተው በራሱ ደካማነት ነው ብሎ ምክንያት መስጠት አይቻልም እግዚአብሔር የሚጠይቀው በማን ተሰናከለ የሚለውን ጭምር ነውና በክርስትና ደግሞ ሰውን ማሰናከል እጅግ የከፋ ኃጢያት ነው፡- 📌 “ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባህር መስጠም ይሻለው ነበር፡፡” (ማቴ. 18፡6)☚☚ አንዳንድ ሴቶች እግዚአብሔር ምን ሰራሽ እንጂ ምን ለበስሽ አይለኝም ይላሉ እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፦ 📌 “እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም ሁሉ እቀጣለው፡፡” (ትን.ሶፎ. 1፡18) አመሰግናለሁ🙏🙏🙏
Jun 28, 2021