Hey I need help guys, its been months since me and my bf broke up but I am still not over him. He just used and abused me and threw me out like I was nothing and I still am not over him. After like almost 10 months and here I am crying over him. Ik like this is a dumb thing to ask gn kemer I am soo sick ...he doesnt even deserve my tears so please if you know methods on how to get over people I need it. Please
Jun 27, 2021emm በደምብ ተረድቼሻለው ታውቂያለሽ ህይወት ዝምብላ የምትሽከረከር ዛቢያዊ እሽክርክሪት ናት ፡ በዙሩ ውስጥ ደግሞ ብዙ አይነት ማንነቶች፣ባህሪያቶች…………ያልዋቸውን ሰዎች ታገናኝሻለች ፡እነዛን ማንነቶች ለማለፋ የምትጠቀሚባቸው መንገዶች ሁሉ ሲቀጣጠሉ እንደ አለት የጠነከረ ማንነትሽ እንዲገነባ ሃይልን ይሰጡሻል። እና እህቴ ይሄንን ጊዜ እንደምታልፊው በመጀመሪያ እመኚ ከዛ ከስር ምፅፍልሽን ለማድረግ ሞክሪ፥ 2.ቀንሽን በምስጋና በውዳሴ ጀምሪ(ፈጣሪሽን አመስግኝው፡ ወደ አምላክሽ ቅረቢ ፡ የ ሁሉም ነገር መፍትሄ ያለው አምላክሽ ጋር ብቻ ነው።) 2.ለቀንሽ ዕቅድ አውጪ (ማንኛውንም ከሱ ጋር እያለሽ ከሡ ጋር ጊዜ ለማሣለፍ ብለሽ የተውሻቸውን ጥቃቅን ነገሮች እንኳን ቢሆን ጀምሪ ( 3.በፍፁም አዕምሮሽ ስራ እንዲፈታ አትፍቀጂለት (የታጠበ ልብስ እንኳን ቢሆን አዉጥተሽ እጠቢ 😊የምሬን ነው።) 4. በፍፁም ከ 11 ሰዐት ጀምሮ ያለውን ጊዜ ለብቻሽ እንዳታሳልፊ አደራ በሰማይ አደራ በምድር(በጣም የተረገመ ሰዐት😂አልፌበታለው ለዛ ነው።ከቤተሰብ ጋር በመቀመጥ፣እምም አዲስ የምግብ አሰራር ወይም የምታውቂውን ስሪ። ሌላው የምልሽ ማወቅ ያለብሽ ነገር ማልቀስ ጥሩ ነው። አዎን በጣም ጥሩ ነው።በእንባ ውስጥ ስሜት አለ፣ህመም አለ፣ሀዘን አለ፣ትዝታ አለ፣ደስታም ጭምር አለ። ሚሰማሽን በጒዳሽ ለማውጣት አትፋሪ ፤ እንባሽ ከመጣ እራስሽን ሳትጎጂ አልቅሺ፡ እንባ ማለት ለኛ ከፈጣሪ የተሰጠ ውድ ስጦታ ነው።ህመማችንን ምሬታችንን ዝግን አርገን የምንቀንስበት።እና እህቴ ለማልቀስ አትፍሪ አውቃለው ያሳለፋችሇቸው የደስታ ጊዜያት ምን ያህል ወደ ሇላ እንደሚስቡሽ፡ታውቂያለሽ ለምን በ 10 ኛው ወር እንዳለቀሽ እስከዛሬ ቁስልሽን በ ፕላስተር አሽግሽው እንጂ አልሰፋሽውም ዛሬ ግን መስፋት ጀምሪ ። ደሞ በህይወትሽ የሚሆነው ሁሉ ለትምህርትሽ ነው። ሁሉ ነገር ለበጎ ነው😊 መልካም ቀን።
Jun 28, 2021