ቅዳሴ ስንት ሰዓት ነው ሚጀመረው ቤተመቅደስ ውስጥ ገብቶ ለማስቀደስ እና በቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ላይ ምእመናኑ ሚሉት ለምሳሌ እንደ እግዚኦ ማረን ክርስቶስ ሚባለው ምን ሰዓት ላይ ነው እና ለምንድን ነው ሚባለው ሌላው ደግሞ ማሕሌት ለመግባት ስንት ሰዓት ነው ቤተክርስቲያን ሚኬደው ደግሞ ለማሕሌት ውስጥ ለመግባት መጾም አለብኝ? ሌላው ደግሞ ማሕሌት ሚገባው ንግስ ካለ ብቻ ነው?
Jun 27, 2021#ቅዳሴ የሚጀመረው ሁልጊዜ ከጠዋቱ 12 ሰኣት (ጾም ያልሆነ ቀን) እና ከቀኑ 6 ሰኣት ነው፣ ሁልጊዜም ቀደም ተብሎ መመጣት አለበት ቢያንስ ከ 1 ሰኣት በፊት ኪዳን ኣድርሶ ተረጋግቶ ለማስቀደስ። #ቅዳሴ ማለት ካህናት አና ምእመናን በህብረት አየተቀባበሉ የሚያደርሱት የጸሎትና የምስጋና ስርት ነው፣ በዚህ ስርዐት ውስጥ ቀዳሾችሁ ካህናት እና አስቀዳሾቹ እመናን የሚወክሉትና የሚያደርጉት የራሳቸው ድርሻ አለ፤ ለምሳሌ የሚቀድሱት ካህናት 5 መሆናቸው ቤተ ክርስትያኗ ለምዕመናኖቿ የምታስተምራቸውን 5ቱን ሚስጥራት (5ቱ ምስጢራተ ቤ/ክ) ይወክላሉ በተጨማሪም አምስቱም ካህናት የራሳቸው ስራ ድርሻ አላቸው ጧፍ(መብራት) የሚይዝ አለ፣ ፍም የሚያመጣ አለ፣ ዣንጥላ የሚይዝ አለ ወዘተ. . . ። በዚህ መሰረት ቅዳሴ ላይ ሁሉም ቀዳሽ ካህናትና ኣስቀዳሽ ምዕመናን የራሳቸው የስራ ድርሻና የሚወክሉት (symbolize የሚያረጉት) ነገር አላቸው ማለት ነወ። ለምሳሌ #ዲያቆኑ ለጸሎት ተነሱ ሲል ህዝቡ ኣቤቱ ይቅር በለን(እግዚኦ ተሳሃለነ) ይላል ይህም ዲያቆኑ የኣዳም ምሳሌ ነው፣ ኣዳም ሲኦል ውስጥ እያለ ሁሉንም ለጸሎት ተነሱ ይላቸው ነበር እነሱም አቤቱ ይቅር በለን ይሉ ነበር ። #ዋናው ቀዳሽ ካህን ሰላም ለሁላችሁ ይሁን ሲል ህዝቡ ከመንፈስህ ጋር ይላል ( እዚህ ላይ ምሳሌው ካህኑ የኢየሱስ ክርስቶስ ነው, ክርስቶስ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞቶ በነፍሱ ሲኦል ገብቶ ከአዳም ጀምሮ አስከ መጨረሻው ሟች ድረስ 5500 ዘመን ሙሉ ሲኦል ጨለማ ውስጥ ታስረው ለነበሩት ሰላም ለሁላችሁ ይሁን ያላቸውን ይወክላል)፣ ህዝቡ ከመንፈስህ ጋራ ይላል (ከመንፈስህ ጋራ፣ እንደቃልህ ይሁንልን ይደረግልን ማለት ነው) ። ለምን ሁሉም በምሳሌ ይደረጋል ቢባል ደግሞ ክርስቲያኖች ሃገራችን በሰማይ ነው፣ ዘላለማዊ ኑሮን የምንኖረው ከሞት ከተነሳን በሁዋላ በመንግስተ ሰማያት ነው ብለን ስለምናምን፣ መንግስተ ሰማያት ላይ ደግሞ ያሉትን ስርአቶች እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ስለገለጸላቸው ለነሱ የተገለጸውን እያሰብን አንደምንኖረው እንደምንወርሰው ተስፋችንን ለማጠንከር እንዲሁም ከዚህ በፊት የተደረጉልንን ነገሮች ሁሉ እንድናስብ ተብሎ ነው። ሙሉ ቅዳሴው ውስጥ የሚባሉት በጠቅላላ ትርጉምና ምሳሌ አላቸው፣ በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ 14 አይነት ቅዳሴወች አሉ ሁሉም የተለያዩና በተለያዩ ጊዜወች የሚቀደሱ ናቸው፣ ቅዳሴ ለማስቀደስ ምን እየተባለ እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል ምን ማለት እንዳለብንም እንደዚሁ ለዚህ ደሞ በርካታ የቅዳሴ መማርያ መጽሃፎች ኣሉ ዜማቸውንም ጭምር ። ለጊዜው ግን ቤተ ክርስቲያን ለማስቀደስ ስንሄድ ትንሽዬ መጽሃፍ አለች የቅዳሴ ተሰጥኦ የምትል እሱዋን ገዝቶ መከታተል ይቻላል። #3. #ማህሌት የሚኖረው ንግስ ካለ ብቻ ነው (ነገር ግን በ ጽጌ ጾም ጊዜ ሁሌ ቅዳሜ ማታ ከ 2 ሰኣት ጀምሮ እስከ 11 ሰዐት ይቆማል ንግስ ኖረም አልኖረም)፥ ለምሳሌ ነገ የ እመቤታችን ንግስ ካለ ዛሬ ከቀኑ 7 ሰኣት ጀምሮ አስከ 10 ሰዐት ድረስ ዋዜማ ይቆማል፣ ምግብ ተበልቶ መግባት ይቻላል፣ ከዛ ማታ 2 ሰዐት ጀምሮ ደግሞ ማህሌት ይቆማል እዚህም ላይ ምግብ ተበልቶ መግባት ይቻላል፣ ለምን ቢባል ተበልቶ የማይገባው ቅዳሴ ከመቀደሱ በፊት ነው።
Jun 27, 2021