ስሜት ማለት ምን ማለትነው? ሰው ስሜቱንስ መቆጣጠር ይችላል? (ስሜት ሚለውን ቃል ከፍትወት ጋ ብቻ አታገናኙ
Jun 25, 2021ስሜት ማለት በሰው ልጅ ህይወት ዉስጥ ትልቅ ድርሻ ያለው ነገር ነው።ስሜት ማለት ሀዘን፣ደስታ፣እንባ፣ሳቅ………የሚሉትንና ሌሎችንምበውስጡ የሚይዝ ነው።ያው ፍትወትም አንድ የስሜት አካልነው አንድ ሰው ስሜቱን መቆጣጠር ከቻለ እራሱን መግዛት ፣ መቆጣጠር ይችላል ማለት ነው። ይሄን ማድረግ ቻለ ማለት ደግሞ ያ ሰው በጣም ጎበዝ ነው። ምክንያቱም ስሜትን እንደመቆጣጠር የሚከብድ ነገር ምንም የለም፡ለምሳሌ በጣም የሚያናድድ ሰው ገጥሟቹ በቃ የንዴታቹ ጥግ ላይ ደርሳቹ ያን ሰው ከመምታት ወይም ከመስደብ ተቆጠባቹ ማለት ስሜታችሁን ተቆጣጠራችሁ ማለት ነው።ይሄ ደሞ ማለት ደሞ ትልቅ ስኬት ነው።አንድ ጊዜ አርቲስት ሳያት ደምሴ የሆነ ኢንተርቪ ላይ ቀርባ ለተጠየቀችው ጥያቄ የሰጠችው መልስ አስደንቆኛል።ጥያቄውም እንዲ ነበር ፦ ላንቺ ትልቁ ስኬትሽ ምንድነው?ነበር እና እንዲ ስትል መለሰች ለእኔ ትልቁ ስኬቴ ምሽት ደርሶ እራሴ ዛሬ ምን አደረግሽ ብሎ ሲጠይቀኝ ምላሽ መስጠት ከቻልኩ ያ ለኔ ትልቁ ስኬቴ ነው።ነበር መልስዋ ዝምብላቹ ስታጤኑት የሰው ልጅ ትልቁ ስኬት የምንለውን ልናገኝ የምንችለውዛሬ በቀን ዉስጥ በምናደርጋቸው ድርጊት ነው። ይሄ ደግሞ ስሜትን መቆጣጠርንም አካቶ ይይዛል ። ስለዚህ ስሜትን መቆጣጠር በደምብ ይቻላል። ይሄን ለማድረግ ደሞ ባካባቢያችን ካለ ሰው መጀመር ይቻላል።ስሜታችንን መቆጣጠር ለመልመድ አብሮን ያለ አንድ ሰው በቂ ነው።ምክንያቱም ከሰው ጋር ስንኖር መጋጨት ፣መጣላት ያለ ቢሆንም ግጭቱን የምናስተናግድበት የግጭቱን ትልቅነትና ትንሽነት ወይም ግጭቱ ወደየት እንደሚያመራ ይወስናል።ሁላችንም የራሳችን ፍላጎት፣ ባህሪ……አለን እና ግጭቶች በሚፈጠሩ ሰዐት እራሳችንን መቆጣጠር የማንፈልገው ነገር ሲደረግብን እራሳችንን ተቆጣጥረን ማስረዳት ።ይሄን በማድረግ ብቻ ነገ ላይ እራሳችንን የሚገርም ስሜትን የመቆጣጠር ደረጃ ላይ ደርሰን ልናገኘው እንችላለን። መልካም ቀን😊😊
Jun 26, 2021