ሰላም🤗 ጥያቄዬ አንድ ሰው ስህተት ወይም ጥፋት ቢያጠፋ ግለሰቡ ብቻውን መወቀስ አለበት ብላቹ ታስባላቹ ?ለዚህ ድርጊቱ መጠየቅ ያለበት እሱ ብቻ ነው ማህበረሰቡስ ፣ ቤተሰብ ፣ ጓደኛ ፣ ሁኔታዎች ጥያቄ ውስጥ መግባት የለባቸውም እስኪ idea share አድርጉ? ሌላ ደሞ ልክ እና ስህተት ሚባል ነገር አለ ? ካለስ ምንድናቸው in ur own word define ብታረጉልኝ አመሠግናለሁ ✨
Jun 24, 2021ነፃ ፍቃድ ምርጫ እና ሃላፊነት ተሰጥቶናል እኔ ስህተት ስሰራ ያለመስራት አማራጭን ትቼ ነው አይደል? እንዴት ነው ደግሞ ነገሮች አንፃራዊ በሚመስሉበት ትክክል የሚባለውን ነገር የምናውቀው ስንል... ከ እምነት ውጪ በሆነ መንገድ ማብራራት ይከብደኛል... ውስጡን ለሚያዳምጥ ሰው ግን ህሊናው ይገዛዋል ልክ ወደሆነውም ይመራዋል እላለሁ... ፍፁም ልክ በ እምነት ውስጥ ነው ያለው አንፃራዊነት ደግሞ ከ እምነት ውጪ ነው... ነፃ ፍቃድ ስላለሽ ምረጪ እንግዲ 😁 ጓደኛ ማህበረሰብ ቤተሰብ እኮ ይጠየቃሉ... ማን ይጠይቃቸዋል የሚለውን ላቆየውና እነሱም አንቺ ስህተት ስትሰሪ እያዩ ዝም የማለት ወይም የማስቆም ምርጫ አላቸው ለዛም ሃላፊነቱን ይወስዳሉ... the same goes for u too እና አንዱ ከ አንዱ ጋር የተሳሰረ ነው እንደፍድፍ ከተባለ አይቻቸው ለማላውቃቸው ሰዎች በምንም አንገናኝም ለምላቸው ሰዎች ሞት ራሱ ተጠያቂ እሆናለሁ ማለት ነው አይደል
Jun 24, 2021