ሰዎች ሰላም ብያለሁ ወደ ጥያቄዬ ስገባ ከነ ህብረቃሉ : ከነ ሰሙ : ከነ ወርቁ በዛ ያለ ግጥም ንገሩኝ please!
Jun 23, 2021አጥር አልታጠረ አልጠፋ መንገድ፤ ምን ያደርግልሻል በሰው ላይ መሄድ። ህብረ ቃል - ሰም- ወርቅ- ይህኛው ፈተና ነው። ዳሽ ሙላ 😜😜😜
Jun 23, 2021ሰዎች ሰላም ብያለሁ ወደ ጥያቄዬ ስገባ ከነ ህብረቃሉ : ከነ ሰሙ : ከነ ወርቁ በዛ ያለ ግጥም ንገሩኝ please!
Jun 23, 2021አጥር አልታጠረ አልጠፋ መንገድ፤ ምን ያደርግልሻል በሰው ላይ መሄድ። ህብረ ቃል - ሰም- ወርቅ- ይህኛው ፈተና ነው። ዳሽ ሙላ 😜😜😜
Jun 23, 2021ፅሁፍህ ግን ለምንድነዉ እንደ ደሀ አጥር የተራራቀዉ🤔
Jun 23, 2021አው! ብትል ጅቦ መች እፈራሃለሁ፤ እኔንም ና ብላኝ ከበሯ ቆምያለው። ህብረ ቃል - ና ብላኝ ሰም - ጅቦ ና እና ብላኝ ወርቅ- ና ብላ ጠርታኝ ከበሯ ቆምያለሁ
Jun 23, 2021I felt this one❤️
Jun 23, 2021በላነው ጠጣነው፡ ከእንጀራ ከወጡ የሴቱን አናዉቅም ወንድ አንድ ሰዉ ምተ.. Y'all finished the line gena tsfe salchers ha😂
Jun 23, 2021Ene assignment sesetachu lekas ezi eyeteyekachu nw memetut. Endewm yehen alyzew wede fetena ekeyrewalew Endaylh astemarie😂😂😂 Kemr gn 1 lngerh Mar kemshe alakm ene wendmachu Yehagere wetatoch temaru ebakachi Hbrekal temaru Sem mar weym honey stugne lkmes Werk tmrtachun temaru
Jun 23, 2021ግጥም ሳይሆን ቅኔ ነው። ቤታችን ተሰርቶ ከመንታ መንገድ እናያለን ሁሉን ሲወጣ ሲወርድ። ህብረ ቃል-ሲወጣ ሲወርድ ሰም- ሲያልፍ ሲያገድም ወርቅ - ሲሾምና ሲሻር
Jun 23, 2021ሞጣ ቀራንዮ ምነው አይታረስ፤ በሬ ሳላይ መጣሁ ከዚያ እስከዚህ ድረስ ህብረ ቃል - በሬ ሳላይ ሰም - በመንገዴ ምንም በሬ አላየሁም ወርቅ - በሬሳ ላይ እየተራመድኩ መጣሁ
Jun 23, 2021አፄ ዮሃንስ እጅግ ተዋረዱ፤ የሸዋን መኳንንት እጅ ነስተው ሄዱ። ህብረ ቃል- እጅ ነስተው ሰም- አጎንብሰው ሰላምታ ሰጥተው ሄዱ ወርቅ- የመኳንንቱን እጅ ቆርጠው።
Jun 23, 2021