ሰላም እንዴት ናችሁ ዉዶች ስለ ኣዲግራት ዩንቨርሲቲ መረጃ ካላችሁ ሽር ኣርጉኝ፥ መጥራት ኣለመጥራቱን? እና ደሞ የሰላሙ ነገር አስተማማኝ ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ ዎይ? አዲግራት የደረሰኝ ፍሬሽ ተማሪ ነበርኩኝ ።ልሂድ ኣልሂድ እያልኩ እየተወዛግውብኩ ነው። ያለውት ባህር ዳር ነው። እባካችሁ ሃሳባችሁን አካፍሉኝ አመሰግናለው
Jun 23, 2021አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያለው ሁኔታ… በትግራይ ክልል በአዲግራት ከተማ በዚህ ሳምንት የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ካፌ አገልግሎት ማቅረብ ስላልተቻለ ተማሪዎቹ በራሳቸው እየሰሩ እንደሚገኙ የተማሪ ህብረቱ አአስታውቋል። የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት በላከው መልዕክትም ተማሪዎች ጊቢው ሰላም በመሆኑ ተረጋግተው እንዲቀመጡ እና እንዳይሰጉ ነገር ግን 1) ከዶርም አስፈላጊ ካልሆነ በቀር እንዳይወጡ 2) ከ3 ሰው በላይ እንዳይሰበሰቡ እና 3) ምግብ ተማሪዎች ራሳችን እየሰራን ስለሆነ ማገዝ የሚፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ ማገዝ እንደሚችሉ መልዕክት አስተላልፏል። ምግብ በመስራት ስትተባበሩ ለቆያችሁ እና አሁንም እያገዛችሁ ላላችሁ የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የቁርጥ ቀን ልጆች የሆናችሁ ተማሪዎቻችንንም እናመሰግናለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡ @MEREJAET @MEREJAETHIO_BOT #SHARE
Jun 24, 2021