ዘረኛ ማለት ወይም ብሄርተኛ ማለት ለናንተ ምን ማለት ነው? ይሄን ጥያቄ ያነሳሁት አንድ ጠያቄ " በዚህኛው ምርጫ ቄሮ እንደድሮው ሚበጠብጥ ይመስላቿል ብሎ ሲጠይቅ የተመለሰለትን መልስ አይቼ ነው። ቆይ ዘረኛ ማለት ምን ማለት ነው? መብቱን ለማስከበር ስለታገለ ነው ቄሮን ዘረኛ ብላቹ የሰየማቹት? ይሄ ህዝብ እኮ በመሬቱ በቀዬው አንተ ጋላ እየተባለ የሚናቅ ህዝብ ከናንተ አላንስም ብሎ በመነሳቱ ነው ዘረኛ ያላቹት? 5000 ልጆቹ በገፍ የተጨፈጨፉበት ይህ ህዝብ ወገኔ አይጨፍጨፍ ብሎ ሰልፍ ስለወጣ ነው ጎጠኛ ብላቹ የምትጠሩት? እስቲ አስረዱኝ? በቀዬዬ ቋንቋዬ እየጠፋ ነው በሚል ቋንቋዬ እና ባህሌ እየተጨቆነ ነው ብሎ ሰልፍ ስለወጣ ነው ዘረኛ ያላቹት? (በኦሮምያ ከተሞች ውስጥ ሚነገረውን ቋንቋ ልብ በሉልኝ) በቤተ እምነት ውስጥ የሚሰራው ስራ የኔን ባህል ያማከለ አይደለም የኔን ባህል እና ቋንቋ ይጨቆናል ስለዚ መቅረት አለበት ብሎ ስለታገለ ነው ዘረኛ ያላችሁት? እስቲ መልሱልኝ
Jun 20, 2021😁 መጀመሪያ ተረጋጋ። ዘር ለይቶ ስለገደለ ነው ዘረኛ የተባለው። መብቴን በሰላም ላስከብር ቢል ኖሮ ማንም ዘረኛ አይለውም ነበር። ችግሩ ክልሉ ውስጥ ያሉትን አቅም የሌላቸውን መሸሻ የሌላቸውን ምንም የማያውቁትን ንፁሃን ዜጎች ግድሏል። ስለዚህ ቄሮ ዘረኛ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ታዲያ ግን ሁሉንም አይውክም። ሲቀጥል ይሄ የኔ እይታ ነው።
Jun 21, 2021