Online nw
Jun 20, 2021Online nw
Jun 20, 2021#ምርጫ2013 የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ድምፅ የሚሰጡት እንዴት ነው? የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በምርጫ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የመራጮች ምዝገባ በኦላይን በዩኒቨርሲቲያቸው እያሉ ሲያካሂዱ ነበር። አሁን ላይ ተማሪዎች ወደቤታቸው ተመልሰዋል በምርጫው እንዴት መሳተፍ ይችላሉ ? ለሚለው ጥያቄ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚውኬሽን ኃላፊ ወዘሪት ሶልያና ሽመልስ ለቲክቫህ ቤተሰቦች ምላሽ ሰጥተዋል። ወ/ሪት ሶሊያና ፥ ተማሪዎች በኦንላይን ምዝገባ ተመዝግበው እንደጨረሱ የተሰጣቸው #የማረጋገጫ_ወረቀት እንዳለ በመጠቆም ተማሪዎች ያንን ማረጋገጫ ይዘው አቅራቢያቸው የሚገኝ የምርጫ ጣቢያ መሄድ እንዳለባቸው አሳውቀዋል። በአካባባያቸው ያለው የምርጫ ጣቢያ በትክክል የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሆነው መመዝገባቸውን ሲያረጋግጥ ድምጻቸውን እንዲሰጡ ያደረጋል ሲሉ አስረድተዋል። ስለዚህ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰኞ ድምፅ ለመስጠት ምን ማድረግ አለባችሁ ? - በኦንላይን ላይ ምዝገባችሁን ያጠናቀቃሁበትን ማረጋገጫ ወረቀት መያዝ ይጠበቅባችኋል። - በመኖሪያ አከባቢያችሁ አቅራቢያ ወደሚገኝ ምርጫ ጣቢያ በማቅናት የማረጋገጫ ወረቀቱን በማሳየት የምርጫ ወረቀት ማግኘት ትችላላችሁ። - ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ እንድትይዙ ይመከራል። @tikvahethiopia
Jun 20, 2021#ምርጫ2013 ‼️ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚመርጡት እንዴት ነው? 🔴የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በምርጫ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የመራጮች ምዝገባ በኦላይን በዩኒቨርሲቲያቸው እያሉ ሲያካሂዱ ነበር። አሁን ላይ ተማሪዎች ወደቤታቸው ተመልሰዋል በምርጫው እንዴት መሳተፍ ይችላሉ ? ለሚለው የበርካቶች ጥያቄ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚውኬሽን ኃላፊ ወ/ሪት ሶልያና ሽመልስ ለቲክቫህ ቤተሰቦች ምላሽ ሰጥተዋል። ወይዘሪት ሶሊያና ፥ "...ተማሪዎች ምዝገባውን ተመዝግበው እንደጨረሱ የተሰጣቸው ማረጋገጫ አለ። ያንን ማረጋገጫ ይዘው አቅራቢያቸው የሚገኝ ምርጫ ጣቢያ መሄድ አለባቸው" ብለዋል። አቅራቢያቸው ያለ ምርጫ ጣቢያም በትክክል የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሆነው መመዝገባቸውን ሲያረጋግጥ ድምጻቸውን እንዲሰጡ ያደረጋል ሲሉ አስረድተዋል። ስለዚህ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰኞ ድምፅ ለመስጠት ምን ማድረግ አለባችሁ ? - በኦንላይን ላይ ምዝገባችሁን አጠናቃችሁበትን ማረጋገጫ ወረቀት መያዝ ይጠበቅባችኋል። - በመኖሪያ አከባቢያችሁ አቅራቢያ ወደሚገኝ ምርጫ ጣቢያ በማቅናት የማረጋገጫ ወረቀቱን በማሳየት የምርጫ ወረቀት ማግኘት ትችላላችሁ። - ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ እንድትይዙ ይመከራል።
Jun 20, 2021