ሰላም ሰዎች እንዴት ናቹህ አንድ የገጠመኝን ነገር ላናግራቹህ / አንድ ልጅ አለች በሆነ አጋጣሚ ተገናኘን ተዋወቅን አወራን ምናምን ሁልጊዜ በፊት አብሯት የነበረው ፍቅረኛዋ እንደዋሻት እንዳስቀየማት እንደበደላት እሷ ግን እንደምትወደው ነበር ምትነግረኝ ወንድ ልጅ ሁሉም አንድ አይነት ነው ብላ ምታወራው እኔ በዚህ መሃል ነበር የተዋወኳት በደንብ እናወራ ነበር እንገናኝ ነበር በዚህ መሃል እኔ ለሷ ያለኝ ፍላጎት ጨመረ(ሳገኛት ሳወራት ደስ ይለኛል በስራ ምክንያት ተናድጄ ተበሳጭቼ ምናምን ስለሷ ሳስብ እደሰታለው) ለኔ ይሄ ማለት ፍቅር ይዞኛል ብዬ አስባለው ግን እንዳልነግራት ለወንድ ልጅ ያላት አመለካከት በሙሉ አንድ አይነት እንደሆነ ነው ሁሌ የምትነግረኝ እና በዚህ ውስጥ ሁኜ ደግሞ እንደማፈቅራት መናገር እሷን ማስጨነቅ ነው የመሰለኝ እኔ ደግሞ በምንም ምክንያት እሷ እንድትጨነቅ አልፈልግም በዚህ መሃል ግን የበፊት ፍቅረኛዋ አብረን እንሁን አላት መሰለኝ ወደሱ የመሄድ ሃሳብ አላት እንዳልነግራት እሷን ማስጨነቅ ሆነብኝ ዝም ብዬ እንዳልተዋት ደግሞ ጨነቀኝ እባካቹህ ምትመክሩኝ ነገር ካለ / በጣም ሚደብር ሙድ ውስጥ ነኝ።
Jun 17, 2021ብትነግራት የተሻለ ይመስለኛል እሷ እልህ ውስጥ ኾና ይኾናል ኹሉም ወንድ አንድ ነው ብላ ያለችኽ ከበፊት ፍቅረኛዋ ጋር ተመለሰችም አልተመለሰች እናት ስለ እሷ ሚሰማኽን ስሜት ንገራት አንተም አትጨናነቅ ኹሉም ሰው አንድ አይነት እንዳልኾነ ግልጽ ነው ይህን እሷ ስሜታዊ ኾና ይኾናል እንደዛ ያለችኽ ፍቅርን ካልተናገሩት/ካልተገበሩት አያስደስትም አፍነኽ ይዘኽ ከምትጨነቅ ንገራት መልካም ዕድል
Jun 17, 2021