በኢትዮጵያ ቋንቋ መናገሩ ጥሩ እንዳለ ሆኖ በዛ ቋንቋ መናገር ብቻ ሀገር ወዳድነት ይገልጻል ማለት ይከብዳል፥ በሌላ ቋንቋ ስለተነገረም በሀገሩ አፈረ አይባልም። እዚ ግሩፕ ውስጥ ያሉትም ለተለያየ መክንያት እንዱን ይጠቀሙበታል። ማለትም፦
- አንዳንድ ጥያቄዎች ለአማርኛ የማይመቹ ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ:- እንግሊዝኛ የCyber፣ የSpace፣ የMedical፣ ባጠቃላይ የአለምአቀፋዊ መግባብያ ነው።
- እንግሊዝኛ የኛ familiar language ስላልሆነ በዛም የቋንቋውን ክህሎት እንድናዳብር ያደርጋል
-እንዲሁም ትግርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ አፍ ሶማሊም ሆነ ሌላ ቋንቋ መጠየቅ ይቻላል። ግን ደሞ አብዛኞቹ የቻነሉ አባላት አማርኛን የሚረዱ በመሆናቸው አማርኛ የሚረዱ እንደመሆናቸው አማርኛን እንጠቀማለን። ግን ደሞ አማርኛንም የማይረዱ እና የሌላ ሀገር ዜጎችም ስላሉ እንግሊዝኛን ይጠቀማሉ።
-አብዛኛው ጊዜ አማርኛ ለመጠቀም ቀላል እንደመሆኑ እንግሊዘኛ ግን 2ተኛ ቋንቋ እንደመሆኑ ትኩረት ይሰጥበታል። ስለዚህ ሰዎች በጥሞና እና በማብሰልሰል እንዲከታተሉት እና እንዲመልሱት ያደርጋል
-እንዳንድ በአማርኛ ለመግለጽ ከበድ ያሉ የተለመዱ ቃላቶችን ለመጠቀምም እንደዛው። ለምሳሌ:- stress, Depression, anxiety, Crush, Nerd ወዘተ
-በአማርኛም ሆነ በሌላው ኢትዮጵያዊ ቋንቋ ለማለት አጸያፊ የሚባሉት ቃላት በእንግሊዝኛው ግን ቀለል እናደርገዋል። ለምሳሌ:- አንድ ሰው Pussy, Vagina, Penis, Dick, Wee-wee, peepee, Shag ሲባል ቀለል እናደርጋለን፥ በአማርኛው ግን ይህ ሁሉን ያንን ብንጠራ ያንን ሰው ከማገዝ ይልቅ በቃላቱ የመዳኘት እድሉ ይሰፋል።
Jun 17, 2021