ሰዎች ራስን የማጥፋት ሀሳብ ደጋግሞ ይመላለስብኛል ቤተሰብ ውስጥ ሰላም የሚባል ነገር የለም ሁሌም ጭቅጭቅ ንትርክ ነው ህይወቴ ባጠቃላይ የተዘበራረቀ ነው:: ታናሽ ወንድሜ የዛሬ 3 አመት ባልታወቀ ምክንያት ራሱን አጥፍቶ ነው የሞተው ከኔ ጋ በጣም እንዋደድ ነበር ሲከፋኝ እሱ ነበር የሚያፅናናኝ እንደወንድም ሳይሆን ከዛ በላይ ነበር የምንዋደደው እሱም እንደዛው ለማንም የማይነግረውን ሚስጥር ለኔ ነበር የሚነግረኝ ::ምንም ቢሆን ትምህርትሽን ጠንክረሽ ተማሪ እያለ ይመክረኝ ስለነበር ለሱ ስል ሳልፈልግ ተምሬ ጨርሼ አሁን ያለስራ ቤት ነው ያለሁት:: አሁን እሁን ላይ ራሴን የማጥፋት ሀሳብ በጣም ይመላልስብኛል youtube ላይ ራሳቸውን ያጠፉ ሰዎችን ታሪክ በጣም አያለሁ :: ትደብቄ ሳይካትሪስት ጋ ሄጄ የሚሰማኝን ሁሉ ነገርኩትና እንደዚህ አይነት ሀሳብ ሲመጣብሽ ስፓርት ስሪ ምናምን አለኝ ግን ምንም ለውጥ የለውም:: አሁን 23 አመቴ ነው ጉዋደኛም ሆነ ፍቅረኛ ኖሮኝ አያውቅም ዘመድ ጥየቃ የቤተሰብ ስብሰባ ምናምን መሄድ አልወድም ባጠቃላይ ክክፍሌ የምወጣው ለሽንት ብቻ ነው ማለት ይቻላል :: በዚህ ሁኔታ እስከመቼ ነው የምቀጥለው? ምን ባደርግ ነው ራሴን የማጥፋቱን ሀሳብ ማቆም የምችለው? ክፍሌ ውስጥ ገመድ ደብቄ እስከማስቀመጥ ደርሼያለሁ እባካችሁ እርዱኝ.....
Jun 15, 2021አትሸወድ ወንድሜ እውነቴን ነው ሰይጣን ነው በብዙ ነገር ይፈትንህና እራስህን እንድታጠፋ ይገፋፋሃል ማንን ደስ ይበለው ብለህ ነው እራስህን የምታጠፋው እንኳን አንተ ስንት ሰው ጎዳና ላይ የሚበላው አጥቶ ይኖራል አይዞህ የማያልፍ ነገር የለም ወደ ቤተ-ክርስቲያን እየሄድክ ፀልይ ስገድ።
Jun 15, 2021