በ Socialism እና Communism በሁለቱ መካከል ስላለው ideology ልዩነት በደምብ ሚያቅ ሰው ቢያብራራልኝ 🙏
Jun 14, 2021ሶሻሊዝም የማህበረሰቡ ልብ ነው። ካፒታሊዝም የማህበረሰቡ ጭንቅላት ነው። ሶሻሊዝም ያመዛዝናል። ካፒታሊዝም ሁሌም ትርፍ ያሰላል። ሶሻሊዝም ለሁለንተናዊ ደስታ ይተጋል። ካፒታሊዝም ለግለሰብ ደስታ ይታትራል። ሶሻሊዝም ሰዋዊ ነው። ካፒታሊዝም ማሽናዊ ነው። በሶሻሊዝም ሰዎች ስሜት ያላቸው ፍጥረቶች ናቸው። በካፒታሊዝም ውስጥ ሰዎች ሆድና ጭንቅላት ያሏቸው ሮቦቶች ናቸው። ሶሻሊዝም ለጋስ ነው። ካፒታሊዝም ስግብግብ ነው። ሰው ያለ ልብ ወይም ያለ ጭንቅላት ሊኖር አይቻለውም። ፅንፍ የወጣ ሶሻሊዝም ወይም ካፒታሊዝም ጣጣው ብዙ ነው። አንዱን ጥሎ ጉዞ አያዋጣም። ሁለቱም በየፊናቸው ተሞክረው አልተሳኩም። ሁለቱን አዳቅለው ሶሻል ዲሞክራሲ የፈጠሩት የምእራብ አውሮፓ ሃገራት የተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። አእምሮም ልብም ያለው ጤነኛ ስርአት የሚወለደው ያኔ ነው።
Jun 15, 2021