ሰላም ሰዎች እንዴት ናቹ ጥያቄዬ ኢትዮጵያ ሚለውን ቃል ለሚጠሉ ኢትዮጵያውያን ነው።ምን መሰላቹ ኢትዮጵያ ለመጥላት ብዙዎቻቹ ምክንያታቹ ኢትዮጵያ የኔን ባህል ቋንቋ ማንነት አልወከለችም እኛን አትመስልም የሚል ነው ልክም ናቹ😔አንዳዶቻቹ እንደው ኢትዮጵያ ወራሪ ሀገራችን ናት የሚል አመለካከት ነው ያላቹ ግን እውነታው እሱ አይመስለኝም ከሺ ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ህዝቦች አሁን ካለው የበዛ ባህል እና ቋንቋ የሰፋ ግዛትም እንደነበራቸው ይነገራል እና የኔ ሀሳብ ለምን ሁላችንም በራሳችን መንገድ ኢትዮጵያ የኛም እንደሆነች አንረዳም ምክነያቱም የኛም አባቶች(የቅርቦቹም የሩቆቹም) ከማንም ያላነሰ አስተዋፆ ነበራቸው ባሪያም ይሁኑ ነገስታት ጦረኝኦችም ይሁኑ እረኞች ሁሉም ኢትዮጵያ በብዙ አስተዋፆ ና መሰዋትነት ጠብቀው ለኛ ለተረኞቹ ሰጠውናል እና ለምን 'ለምሳሌ'🤔 ኦሮሞ ኦሮሚያ ከሚል ኢትዮጵያ ብሎ ባህሉን ቋንቋውን ማንነቱን በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ የነበረውን ትልክ ድርሻ ኢትዮጵያን እግዚአብሔር እንጂ ማንም እንዳልሰጠው በማሳወቅ ለመስራት አይሞከርም መቼም ኦሮሚያ ሀገሬ ማንነቴ ኦሮሙማ ብቻ ነው ከሚል አመለካከት ሚሻል ይመስለኛል ኦሮሞ ያልኩት ለምሳሌ ነው በየራሳቹ በተለያየ መንገድ አስቡት። ደሞ እንዳትሳደቡ አደራቹን።
Jun 14, 2021This is my idea..... #የአረም ክምሮች የኔው ጉድ እያለ ያንቺን ቤት ነው ማየው አንቺም የለሽበት ቀልብሽ እሱ ጋር ነው እሱም አካሉ እንጂ ሀሳቡ ሌላ ቤት የትም ላያደርሰን እንደው ከንቱ ልፋት የኔ ግንብ ሲፈርስ የሱን ጣራ መክሰስ እኔው ለቸገረኝ የሱን ስራ መውቀስ ከፍቶኝ ሳለቅስ ደሞ የነሱን ሳቅ መጥላት ማሳዬ ሲውድም የትዬን ከብት ማጥፋት ደግነት ሲያሳይ መተርጎም በክፋት ተግባሩን ጠቅልሎ መፈረጅ ከጥፋት ችግሬን ከሰው ጋር አያይዞ ማጉላት ሲቀስሩ ጣትን ያለምንም ሀፍረት የነገሌ ቤት ውስጥ ቢፈጠር ሀዘን በገዛ ስራቸው ያመጡት ነው ብለን ማጽጽናናቱን ትተን እንገባለን ማማት ማጣቱ እያለ ሌላ የራስ ምታት የኛ ሰው ሲሞት ግን ነገሩ ይለያል ታላቅ ጀብዱ ሰሪ የሀገር ባለሟል መጥታቹ ቅበሩ ይኸው ዛሬ አልፏል እማማ ሀገሬ ጉድ ፈላብሽ ምነው እንዴትስ ትሆኚ አትሽው ይሄን ሰው ያገሬ ሰው ጽና አሁን ነው ፈተናው ላንዱ ያነባ አይን ሲደርቅ ለሌላው ለሱ ያዘነ አንጀት ለሷ ሚጨክነው ለነዛ መርቆ እነሱን ሚረግመው ከፊሉን ቀድሶ ቀሪውን ሚያረክሰው እኔስ ግራ ገባኝ ምንድን አግኝቶት ነው አንግዲህ ይታይሽ አንቺ የኔ አናት የተወለድኩብሽ ከምድርሽ እምብርት ሀዘንሽ ምነ ከፋ ሲፋጩ ከላይሽ አሳድገሽ ከንቱ ያሁሉ ልፋትሽ ከመሬት ሲላወስ እንደው ምን ተሰማሽ አኔኮ ሚገርመኝ እኛ ሚሉት ነገር የኛ ህዝብ ተጎድቷል መብታችን ይከበር እስካሁኗ ሰዓት ብዙ ተጨቁነን ሲዘንብብን በደል እንደምንም ችለን ለዛሬ በቅተናል አምላክ ሆይ ተመስገን ደም እንመልሳለን ደርሷል ተራችን ይቅርታ ምንድነው ለሞተው ሬሳችን ብለው ይነሱና ድጋሚ ዘመቻ ማለቂያ የሌለው ማይቆም በመባቻ ይሄ ሁላ እያለ ምኑን ሰላም ሆነሽው ላንቺ እኔ አዘንኩ በምን አንጀት ቻልሽው እቴ በምን እዳሽ በምን አቅም ቆምሽው አስታማሚ ጠፍቶ ብቻሽን ታመምሽው እኛነት ጠፍቶብን እኔነት ነግሶብን በዋል ፈሰስ ስንኖር ትርጉም እያዛባን በራሳችን አለም ስንጣላ ከርመን የገዛ ሀገሩን ያንተ አይደለም እያልን አያርገውና እንደው ቢነሳ ጦርነት ማን ሄዶ ሊመክት ጠላትን በህብረት ማንስ ሊዘምትልሽ ቆሞ ከጠላት ፊት እኔ ሲመስለኝ ግን ማን ይሂድ በሚለው ውስጥሽ ይታመሳል ምን ተሻለን እንደው ልክ እንዳለፈው እንደ ወርቃማው ክስተት ልባችን ላይ እንዳለው የዓድዋ ጦርነት ማን ተቆርጦ ሊጣል ከጀግንነት ሜዳ ለብቻ ነጣጥሎ ዘር በሚሉት ባዳ አይናችን ይከፈት እንንቃ እንጂ ወገን እኛ እሚለው ቃል እኛን ካልገለጸን ችግሩ ከቃሉ አሊያም አኛው ነን መፍታት ቢያቅተን እንቅፋት አንሁን የገዛ አካሉን ሚመታ እንደሌለው ያንዱ መጎዳት የሌላው ህመም ነው በሽታው ወረርሺኝ ተዛማች በፍጥነት ካልነኩት አይነካ ጨዋ ነው በእውነት አደጋውን አይተው አሉት ዘረኝነት ከያዘ አይጣል ነው ያደርሳል እስከ ሞት በራስ ወዳድነት ሚጀምረው ልክፍት ስምን እየለየ መውደድና መጥላት መሰረት አድርገው የብሄርን አይነት ቋንቋን እየለዩ ያደርሳሉ ውድመት እልፍ አዋቂ መጥቶ ላይቀየር ነገር ፈለግን አልፈለግን የዘራችን መስመር ብናጠፋ ህይወት ተስማርተን በመስክ ፍትህ ላይሟላ ቆጥረን በሞተው ልክ አዲስ ቂም ልንፈጥር ያለውም አልበቃን መቼ ይሆን ታዲያ ልቦና ሚኖርን እሱስ ምን ይለናል ታላቁን እንፍራ! ከአንድነት ወጪ የለም መታፈሪያ ሚያዘልቀው ህብረት ሁሌም ልብ እንበል ከዛ ውጪ ያለው ንጦ እንደ ማዕበል በየዳሩ ድንበር ያሽቀነጥረናል ያኔ ለመመለስ ዘመን ያልፍብናል የጥንቸሏ ታሪክ በኛ ይደገማል By: Hypocrite_writer
Jun 14, 2021