Ok my Q there is this guy who told me he loves me to death and been through a lot to get my heart and attention😒 but I rejected him cuz I didn't want to date someone who have not the same religion as I have . but finally I fall in love with him I don't know what to do all I wanna see,hear ,touch beka esun hone eventhough i know I'm not gonna end up with him . ena the main problem is endafekerkut siyawk he stops treating me well beka ignore yaregegnal, I'm the one who always call mnamn he literally becomes cold. ena beka we aren't meant for each other I have to move on mnamn bye lifen sketl yimetana beka hasaben hula yaskeyregnal keza dgame abrew shonn demo yaskeymegnal...የሆነ ወይ የማይመጣ ወይ የማይሄድ ሲርቁት የሚከተል ሲቀርቡት ደሞ የሚርቅ ሠዉ ምንድነው አላማው
Jun 14, 2021ከፍቅረኛዬ ጋር የተለያየ ኃይማኖት እንዳለን ሳውቅ ግንኑነቱን አቆምኩኝ፣ እሷ ግን አልተዋጠላትም፣ ምን ላድርግ? ጥየቄ፡- ዶክተር እንዴት አመሸክ? በመጀመሪያ ስለምታደርገው ነገር እግዚአብሄር ውለታህን ይክፈልክ፡፡ በመቀጠል ዶክተር አንድ ጥያቄ ነበረኝ:- ከአንዲት ልጅ ጋር በአጋጣሚ ተዋውቀን ነበር እናም ስልክ ተቀያይረን ማውራት ጀመርን፡፡ ሁለት እና ሶስት የሚሆን ግዜ ተገናኝተን አውርተናል ለአንድ ወር ያክል ከዚያ በአጋጣሚ ስለ እምነት ማውራት ጀምረን፡፡ የተለያየ እምነት ተከታዮች ነን፡፡ ይሄን ስሰማ ጓደኝነቱን አቆምኩኝ፣ ለሱዋም ነገርኩዋት ግን ልትረዳኝ አልቻለችም፡፡ መጀመሪያ ሠሞን ሀሳቤን ነግሬአት ተማምነን ነበር ግን ልጅቷ ስልክ መደወሉን አላቆምም አለች፡፡ እኔ በህትነት ነው የማወራት አናም በተደጋጋሚ በመደወል ስታጨናንቀኝ ስልኳን ብሎክ አደረኩት፡፡ አሁን ሳላገኛት ስድስት ወር አልፎኛል እሷ ግን ጭራሽ እየባሰባት ነው፡፡ ያልኳትን ሁሉ ረስታ አብረን መሆን አለብን ትላለች፡፡ እኔ ደግሞ ከዛሬው ይልቅ ነገ ከባድ ነው፣ የተለያየ እምነት ሆነን አብረን አንቀጥልም የሚል እምነት ነው ያለኝ፡፡ እና ዶክተር ምን ላድርግ? ምክንያቱም ዶክተር በኔ እምነት ነገ ላይ አንድ ላይ እየኖሩ በእምነት ጉዳይ አለመግባባት መፈጠሩ አይቀሬ ነው ለዛም ነው ብዙ ሳንሄድ ማስቆም የፈለኩት፡፡ መልስ፡- ያነሳኸው ጉዳይ በፍቅረኞች መካከል ሊኖሩ ከሚገባቸው የመመጣጠን ሁኔታዎች አንዱን ነው ይኸውም “መንፈሳዊ (የእምነት) መመጣጠን”፡፡ በቅር ባሳተምኩት መጽሐፍ ውስጥ ይህንን ሃሳብ አስመልክቶ የሰጠሁትን ማብራሪያ ላስፍርልህና በዚያ መሰረት ውሳኔህን ወሰን፡፡ ማስታወሻ፡- ለወጣቶች በመመጣጠን ጉዳይ ላይ ትምህርት ስሰጥ ከሚነሱ ጥያቄዎች አንዱ “መመጣጠን” በሚለው ሃሳብ ውስጥ “መንፈሳዊ” ዘርፍ እንዴት ይታያል የሚል ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በርካታ ሰዎች የሚያነሱት ጥያቄ ነው፡፡ በተለይም እንደእኛው አይነት የተለያዩ አንጋፋ ኃይማኖቶች በአንድነትና በመዋደድ በሚኖሩባት ሃገር ውስጥ ሊነሳ የሚገባው ሃሳብ ነው፡፡ የጥያቄው መነሻ፣ “አንድ ሰው በመንፈሳዊ እምነቱ ወይም በኃይማኖቱ የሚመጥነውን ሰው ማግባት የለበትም ወይ?” የሚል ነው፡፡ የዚህ ጥያቄ ወሳኝነትና ተግባራዊነት ሊካድ አይቻልም፡፡ በፍቅር ጅማሬ ወቅት በእምነታቸው የተለያዩ ሰዎች የፍቅርን ጎዳና ሲጀምሩ ምንም እንኳ በጉዳዩ አምነውና እርስ በርስ ተማምነው ቢጀምሩም ከሁለቱም ወይም ከአንዱ ወገን የሚመጣ የቤተሰብ ሃሳብና ጣልቃ-ገብነት ካለመመጣጠን የሚመጣውን ውጥረት አንድ ብሎ ያስጀምራቸዋል፡፡ ብዙ ወጣቶች ካላቸው ፍቅር የተነሳ ይህንን ውጥረት ቢያልፉትም በወቅቱ የተነሳውን የውዝግብ ዘር ይዘው ወደትዳር ስለሚገቡ ጉዳዩ እንደገና የማገርሸቱን አደጋ እንደተጋፈጡ ይኖራሉ፡፡ እምነትን በመለማመድ ወቅት ሰዎች እንደ እምነታቸው አይነት የተለያዩ ቀናትን ኃይማኖታዊ ስርአታቸውን ለመፈጸም ወደ “ቤተ-እምነታቸው” ይሄዳሉ፣ አንዳንዴም ስርአቱ እቤታቸው ድረስ ይመጣል፡፡ ይህ ልምምድ የተለያየ እምነት ባላቸው ባለትዳሮች ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ያለው ባይመስልም፣ በትዳር አንድ ወደመሆን የመጡ ሰዎች የየራሳቸውን እምነት ፍለጋ በየራሳቸው አቅጣጫ የመሰማራታቸው ጉዳይና እንዲሁም ቤታቸውን አንኳኩቶ የሚመጣው ጉዳይ በየጊዜው ከዚያ ጋር የተያያዙ ማብራሪያዎች የመለዋወጡ ድግግሞሽ ግንኙነቱን አድካሚ ሊያደርገው ይችላል፡፡ በልጆች አስተዳደግ የተለያዩ ኃይማኖት ያላቸው ባለትዳሮች ቀስ በቀስ ከሚጋፈጧቸው ውጥረቶች መካከል ረጅም ርቀት የሚሄደው የልጆች አስተዳደግ ጉዳይ ነው፡፡ ልጆች ገና ከተወለዱበት ቀን ጀምሮ እስከመጀመሪያዎቹ ወራቶቻቸውንና አመቶቻቸውን ድረስ የእናታቸው ተጽእኖ እንደሚያይልባቸው ይታወቃል፡፡ ሆኖም፣ ቀስ በቀስ እያደጉ ሲሄዱ የአባት ተጽእኖ ግልጽ እየሆነ መምጣቱም አይቀርም፡፡ በዚህ ጊዜ ልጆቹ ከሁለቱ እጅግ በጣም ከሚወዷቸው ቤተሰቦች መካከል የማንን ኃይማኖት እንደሚከተሉ የራሳቸውን ምርጫ ማድረግ አለባቸው፡፡ ይህ ሂደት በእነሱ ትንሽ አእምሮ ውስጥ ይህ ነው የማይባል ጫና ያሳድራል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ አብዛኛዎቹ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደራሳቸው እምነት የመሳብ ፍላጎት ስሚያድርባቸው በሁኔታው አማካኝነት ውጥረት መፈጠሩ አይቀርም፡፡ ከእነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት ነጥቦች በተጨማሪ የእምነት ጉዳይ በገንዘብ አያያዝ፣ በችግር አፈታትና በመሳሰሉት በየእለቱ የትዳር አጋሮች አብረውና ተባብረው በሚጋፈጧቸው ጉዳዮች ላይ ያለው ጣልቃ-ገብነት ቀላል አይደለም፡፡ ስለሆነም፣ ወደ ፍቅር፣ አልፈው ደግሞ ወደትዳር ለመሄድ የሚፈልጉ ሰዎች ይህንን የመመጣጠን ዘርፍ በሚገባ አስበውበት ሊወስኑና ሊገቡ ይባቸዋል፡፡ ይህንን ማድረግ የሚጠቅማቸው ያላቸው ፍቅር ላይ ብቻ ከማተኮራቸው የተነሳ ልዩነታቸው ሊያስከትል የሚችለውን ችግር ችላ እንዳይሉ ነው፡፡ እዚህ ላይ የተለያየ እምነት ኖሯቸው በተሳካለት የትዳር ሕይወት ያሳለፉና በማሳለፍ ላይ የሚገኙ ባለትዳሮችንም ተሞክሮ በምክር መልክ ማዳመጡ የሚበረታታ ነው....
Jun 14, 2021