ሰላም ጋይስ ትላንት ነው 23 አመቴን ያከበርኩት እና ከ 19 አመቴ ጀምሮ አብራኝ የነበረችውን ፍቅረኛዬን ኤፍቢዋ ላይ ባየሁት ነገር ለሷ ያለኝ አመለካከት ሁሉ ባንድ ጊዜ ተቀየረ ። ነገሩ እንዲህ ነው አንድ ቀን ወይን ጠጥተን ሰክራ በስልኬ ኤፍ ቢ ተተቀመችና ሎግአውት ሳትለው ወጣች...ማታ ከተለያየን በኋላ ኤፍ ቢ ስከፍት የሷ አካውንት ነው ... መፃፃፊያ አይከን ላይ ከ 20 በላይ ሜሴጅ እንደገባላት ያመለክት ነበር እና ለማየት ጓጉቼ ስከፍተው ሁሉም ወንዶች ናቸው በጣም ከብዙ ወንዶች ጋር ታወራለች...ማውራቷ አደለም የከነከነኝ ስልኳን ትሰጣቸዋለች ፣ ለኔ የምትጠቀመውን የፍቅር ቃላቶች ለብዙዎቹ ትጠቀማልች ካንዱ ጋር ሁላ ቻት ሴክስ አድርጋለች እና ያየሁትን ሁሉ ነገርኳት ለሙድ ነው አለችኝ... ስለማፈቅራት እንድትተው ነገርኳት እንጂ ሌላ ምንም እርምጃ አሎሰድኩም ነበር እሷም እሺ አለችኝ እንጂ የተወች አይመስለኝም ...ከዚ በላይ አላርዝምባቹ እና ላምናት አልቻልኩም በቃ ምን እንደምወስን ምን እንደማደርግ ግራ ገብቶኛል። ቀናተኛ ወንድ ሆንኩ... አሁን በትንሽ ነገር መጨቃጨቅ ነው ... ልለያት እፈልጋለሁ ግን የሆነ ነግር ይዞኛል ... ሴክስ ስለምናደርግ ይሁን ?.... ስለማፈቅራት ይሁን ? ግራ ገብቶኛል... ጋይስ የናንተ ምክር ያስፈልገኛል....! ጥሩ መካሪዎች እስቲ የሆነ ነገር በሉኝ🙏
Jun 13, 2021ከሚወዱት ሰው መከዳት ከባድ ነው ግን እቺ ሴት ላንተ አትሆንህም Chat sex ቀላል ነገር አደለም የፍቅር ቃላት መጠቀሙም አንተ ራስህን አሳምነህ ከሷ ለመለየት ሞክር ላንተ የተሻለውን ፈጣሪ ይሰጥሀል እሷም የሚወዳትን በማጣቷ ይፀፅታታል
Jun 13, 2021